Thursday, November 19, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
የወልቃይት ህዝብ ለነፃነቱ ሊታገል ከመቸውም ጊዜ በላይ ቆርጦ በአንድነት መነሳቱ ታወቀ፡፡
የወልቃይት ህዝብ ህወሓት ገና ከሽፍትነቱ ጀምሮ ተደጋጋሚ ግፍና በደል ያደረሰበት በመሆኑ መቸም የማይፈታ ቂም አለው፡፡ ህወሓት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ደግሞ ሳይፈልግ ከጎንደር እንዲገነጠል ተደርጎ ወደ ትግራይ ክልል በመጠቃለሉ ሲያነሳው የቆየው ያልተመለሰ ጥያቄ አለው፡፡
ህወሓት የወልቃይት ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የጀመረውን የነፃነት ትግል እንቅስቃሴ ጦር ኃይሉን ተጠቅሞ ለመደፍጠጥ ወደ አካባቢው ያለማቋረጥ ሰራዊት እያዘመተ አሰቃቂ የህዝብ ጭፍጨፋ በማድረግ ዘር ማጥፋት ፈፅሟል፡፡
ሆኖም ህወሓት የወልቃይትን ህዝብ በጥይት በመግደል ዝም ማሰኘት ሳይችል ቀርቶ ዛሬ የበለጠ ተደራጅቶበት ጠብመንጃውን ወልውሎ በአንድነት ተነስቷል፡፡ ወደ በረሃ እየወረደ አርቨኞች ግንቦት 7 እያፋፋመው የሚገኘውን አርበኝነት የሚቀላቀለውም ከዕለት ዕለት ቁጥሩ በእጅጉ አይሏል፡፡
ከሰሞኑ ደግሞ የወልቃይት ሰው ማር ዘነብ ልዩ ቦታው ቴፍ ላይ በመሰባሰብ ስለነፃነቱ መክሯል፤ የትግል መሪዎቹንም መርጧል፡፡ በጉባኤው ላይ የአርማጭሆ ህዝብም ተገኝቶ በጋራ ጠላታቸው ላይ የተባበረ ክንዳቸውን ሊያሳርፉ ቃል ተገባብተዋል፡፡
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)

Wednesday, November 18, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
የወልቃይት ህዝብ ለነፃነቱ ሊታገል ከመቸውም ጊዜ በላይ ቆርጦ በአንድነት መነሳቱ ታወቀ፡፡
====================================================
የወልቃይት ህዝብ ህወሓት ገና ከሽፍትነቱ ጀምሮ ተደጋጋሚ ግፍና በደል ያደረሰበት በመሆኑ መቸም የማይፈታ ቂም አለው፡፡ ህወሓት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ደግሞ ሳይፈልግ ከጎንደር እንዲገነጠል ተደርጎ ወደ ትግራይ ክልል በመጠቃለሉ ሲያነሳው የቆየው ያልተመለሰ ጥያቄ አለው፡፡

ህወሓት የወልቃይት ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የጀመረውን የነፃነት ትግል እንቅስቃሴ ጦር ኃይሉን ተጠቅሞ ለመደፍጠጥ ወደ አካባቢው ያለማቋረጥ ሰራዊት እያዘመተ አሰቃቂ የህዝብ ጭፍጨፋ በማድረግ ዘር ማጥፋት ፈፅሟል፡፡
ሆኖም ህወሓት የወልቃይትን ህዝብ በጥይት በመግደል ዝም ማሰኘት ሳይችል ቀርቶ ዛሬ የበለጠ ተደራጅቶበት ጠብመንጃውን ወልውሎ በአንድነት ተነስቷል፡፡ ወደ በረሃ እየወረደ አርቨኞች ግንቦት 7 እያፋፋመው የሚገኘውን አርበኝነት የሚቀላቀለውም ከዕለት ዕለት ቁጥሩ በእጅጉ አይሏል፡፡
ከሰሞኑ ደግሞ የወልቃይት ሰው ማር ዘነብ ልዩ ቦታው ቴፍ ላይ በመሰባሰብ ስለነፃነቱ መክሯል፤ የትግል መሪዎቹንም መርጧል፡፡ በጉባኤው ላይ የአርማጭሆ ህዝብም ተገኝቶ በጋራ ጠላታቸው ላይ የተባበረ ክንዳቸውን ሊያሳርፉ ቃል ተገባብተዋል፡፡

ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት” ረሃቡን በሚመለከት የስራ እቅዶችን አውጥቷል

ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት ከተቋቋመበት ወቅት ጀምሮ ለኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ በያሉበት ለሚደርስባቸው ግፍና ችግር ያልተቆጠበ ጥረት በማካሄድ ላይ ይገኛል። በዚሁ መሰረት በሳውዲ አረቢያ፤ በየመን፤ በሊቢያ፤ በኬንያ፤ በሰሜን ሱዳንና በማላዊ ችግር ለገጠማቸው ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የገንዘብ፤ የዲፕሎማሲ፤ የምክርና ሌሎች ድጋፎች አድርጓል። ይኼ ግዙፍ ድጋፍ ስኬታማ ሊሆን የቻለበት ዋና ምክንያት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በያሉበት የገንዘብ ድጋፍ ስላደረጉ ነው። ድርጅታችን እነዚህን ደጋፊዎች ያመሰግናል።
አሁን የተከሰተውን የድርቅ ረሃብ፤ ቢቢሲ የተባለው ድርጅትና ሌሎች ተቋሞች ከዛሬ ሰላሳ ዓመታት በፊት “ከተከሰተው የድርቅ ረሃብ የማያንስና አሳሳቢ ነው” ያሉትን ረሃብ በሚመለከት ድርጅታችን መረጃዎችን ሰብስⶅ የችግሩን ጥልቀትና ስፋት ተገንዝቧል። የስራ እቅዶችን አውጥቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት “እኔ ራሴ እወጣዋለሁ” ያለውን ብናውቅም፤ በሌላ በኩል የችግሩን መጠን በመረዳት መንግሥት ለተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድርጅት፤ ወዘተ እና በያሉበት ለኢትዮጵያዊያን ያቀረበውን የድጋፍ ጥሪ በጽሞና ተመልክተነዋል። የተጎዱት ወገኖቻችን ቁጥር ወደ አስራ አምስት ሚሊየን እንደሚደርስ መታወቁ ብቻ ሳይሆን፤ በእኛ ግምትና ግንዛቤ በድርቅ ረሃብ ምክንያት አንድ ህጻን፤ አንድ እናት ወይንም አንድ አባት መሞት የለበትም።

Tuesday, November 17, 2015

በእንቅርት ላይ ጀሮ ደገፍ 
።።።።።።።።።።።።

በማይጨው ከተማ ከ105 በላይ ቤቶች ለከተማ ውበት በሚል ሰበብ እየፈረሱ ነው።
በማህበር ተደራጅተው፣ በራሳቸው ቤት የሰሯቸውና የብረታብረት፣ የእንጨት ስራ፣ ጋራዥ፣ ቁርስና ሻሂ፣ የተለያዩ ሸቀጦች የሚሰራባቸው ቤቶች በሃይል እየፈረሱ ነው።

በነዚህ ቤቶች ሲሰሩ የነበሩ ወጣቶችና ቤተሰቦች ያለ ካሳ፣ ያለ ቅያሪ መስርያ ቦታ እንዲያፈርሱ እየተገደዱ ነው።
ቤታቸው የፈረሰባቸው ወጣቶች ስራ ኣጥተው ለስደት እንዲሄዱ እየገፋፏቸው ይገኛሉ። ቆየት ብሎም የሚሰደዱ ወጣቶች በኣቋራጭ ለመበልፀግ የሚል ቅጥያ ይሰጣቸዋል።
በእንቅርት ላይ ጀሮ ደገፍ እንደሚባለው ህዝቡ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ እየተሰቃየና እየሞተ ባለበት ሰዓት ቤቱ ፈርሶ በረሃ ላይ እየጣሉት ነው።
በሌላ ዜና 
።።።።።።

በራያ ዓዘቦ ወረዳ ሓደ ኣልጋ ቀበሌ ኑዋሪ የሆኑት የዓረና ኣባላት " ለናንተ የሚሆን እርዳታየለንም ዓረና ይስጣቹ " በሚል ምክንያት የእርዳታ እህል ከሚታደልበት ጨርጨር ተባረዋል።
ሑመራ
።።።።

በቃፍታ ሑመራ ኣደባይ ቀበሌ ሕለት ኳኳ ትምህርት ቤት 80 ተማሪዎች በድርቅ ምክንያት ትምህርታቸው ኣቋረጡ። ሕለት ኳኳ የኩናማ ብሄረሰብ በብዛት የሚንርባት ስፍራ ነች።
በምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሑመራ ወረዳ ድርቅ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ህዝቡ ኣስቸኳይ እርዳታ እየጠየቀ ነው።
EthiopiaFamine

ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO.

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) የህወሓት አገዛዝ ወጣቶችን ለውትድርና አስገድዶ ማፈስ ጀመረ፡፡ ====================================================

የቀበሌ አስተዳዳሪዎችና የማዘጋጃ ቤት ሹሞች አስረኛ ክፍል ጨርሰው ስራ ፈትተው የተቀመጡትን ወጣቶች እንዲሁም ዘጠነኛ ክፍልን በመማር ላይ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶችን ጭምር "በ5000 ብር ደመወዝ ስራ እንቀጥራችኋለን" በሚል ማማለያ አሽበልብለው በስልጠና ስም ባንድ አዳራሽ ውስጥ አጉረው በፖሊስ በማገት በመጨረሻም ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ጭነዋቸዋል፡፡
ለውትድርና በግዳጅ የታፈሱት በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ዕድሜያቸው ከ15-18 ዓመት የሚደርስ ሲሆን አብዛኞቹ የጎንደር ወገራ ወረዳ ጉንትር፣ ጭልፎ ወንዝና ሚጧ ቧግሽ የሚሰኙ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ናቸው፡፡
እንዲሁም በተጨማሪ የህወሓት አገዛዝ በአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ወጣቶች በአንድ ሰፊ ግቢ ውስጥ አሽጎ አግቷቸው ይገኛል፡፡ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከሎችም በቅርቡ ሊጭናቸው እየተዘጋጀ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በከፋተኛ ትምህረት
ተቛማት የሚማሩ ተማሪዎች መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲያቛርጡ በማስገደድ የገዢው የኢህአዴግ ስረአትን የሚከተለው ፓሊሲና እስትራተጂ እንዲሰለጥኑ እየተደረገ መሆኑን ተገለፀ።

ክፉ ቀንና መንስኤው ወያኔ!

ethiopian-famaine-998x1024ከሰዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን
“ክፉ ቀን” የሚለው ሥያሜ ሀገራችን ካየቻቸው አስከፊና ሕዝብ ያለቀባቸው ረሀቦች ዋነኛው እንደሆነ ይነገራል፡፡ የሚገርመው ይህ በአስከፊነቱ የሚታወቀውና ሕዝብን በተለይም እንስሳትን ምጥጥ አድርጎ የፈጀው ረሀብ ግን የተከሰተው በድርቅ ወይም በአየር መዛባት ምክንያት አልነበረም፡፡ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ቅኝ ለመያዝ ሲያስብ ቅኝ ገዥዎች በአፍሪካና እስያ በቀላል ግጭት ቅኝ ሀገር መያዝ እንደቻሉ ሁሉ በኢትዮጵያ ይህ መልካም ዕድል እንደማያጋጥመው ጠንቅቆ ዓውቆት ስለነበር ሐበሻን ለማንበርከክ ጦርነት መግጠሙ የማይቀር ከሆነ አስቀድሞ የኢትዮጵያንና የመንግሥቷን አቅም ለማዳከም የሚያስችል ስልት መንደፍና መተግበር እንዳለበት አምኖ አቅድ ነደፈ፡፡ አንዱና ዋነኛውም የሀገሪቱ ሀብት የሕዝቡ አቅም መሠረት የሆነውን ግብርናዋን ማሽመድመድ አከርካሪውን መስበር ነበር፡፡