እርግማን የበቀለበት፣ እንደ ሙታን ያንቀላፋ፣
ከጠባብና ከሆድ ቁራኛ ያልተላቀቀ ገንዘብ አፍቃሪ ሞራል የሌለው ድንባዣም ሲሆን የሰለጠነና ያወቀ
መስሎት ለወያኔ ሊዘፍንና ሊያቅራራ ይሞክራል።ወያኔ አገር እያለማና ህዳሴ እያደረገ ነው ብሎ፤ የአገር
ጠላት፣ ኢትዮጵያ የመቶ አመት ዕድሜ ብቻ ያላት ክልል አድርገው፣ ኢትዮጵያዊነትን አቃለውና ሰንደቅ
ዓላማዋን አራክሰው ያቀረቡ ባንዳዎችን ማወደስ፣ በወያኔ በር ላይ መቆምና መለፍለፍ የለየለት ባንዳነት
ቆሻሻና ትቢያ ሰው ነው።
ስማ ታደሰ ! አይገባህም እንጂ ወያኔን መደገፍና ከሱ በር ሥር መገኘት፣ ለነሱ ሙታኖች ማልቀስ
ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነትንና ሰንደቅ ዓላማችንን ጥላሸት እንደመቀባት ነው።ከባንዳ መተባበር ፖለቲካ
ሳይሆን አገር ክህደት ትሪዝን ነው ።ይህ ደግሞ ወንጅል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፋረደው ነው። ዛሬ
ወግነህ የቆምክለት ወያኔ፣ አገር ያጠፋና መሬት እየሸጠ፣ የሕዝብ ደም እያፈሰሰና እያወከ ያለ ጠላት ነው።
ይህ ቅሌትህ ሊያሳፍርህና ሊያስፈራህ ይገባል። ቅል ራስ በመሆንህ ባዶ ጭንቅላትህ የሚያስበውና
የሚነገርህን በደንቆሮ ጆሮህ የምትረዳው፣በእውር ዓይንህ የምታየው ስለሆነ ነው።
ሰው መሳይ በሸንጎ ! አድርባዮች ወያኔን ቅቤ ለመቀባት፣መልካምና ልማት አመጣ የምትሉት ያን ቀበርቾ
ሆዱህን ለመሙላት እንጂ የወያኔን አጥፊነትና ሌብነት ጠፍቶህ አይደለም።ዳሩ ግን ይህ ወስላታ ሥራህና
የባንዳ አሽከርነትህ ምናልባት ከዘመዶችህ የቀሰምከው ይሆናል።ክህደት ለአንዳንዱማ የዘር ነው።አባቱ
ለጣሊያን ልጁ ደግሞ ለወያኔና ለሻቢያ በዳረጐትና በሆድ ድለላ የተያያዘው አለቅላቂና አሾክሻኪ፣ ሰላዮና
ሰላቢው ፈልቷል።
ታደሰ ኰስትሬ ቅሌታም ቅብጥርጥሮችን የወሬና የአሉባልታ አሽቃባጭነት በአልተገረዘ ምላሱ በወያኔ
ቲቪና ራድው አወቅሁ አወቅሁ ብሎ ፊት ፊት እያለ ነው። ባንዳነት በታደሰ ስም እየተዛመተ የባንዳ ባህሪ
ልምድ ልጓም ሆኗል።ጉዶች፣እርጉሞች፣ሃሰተኞች በየጊዜው አታጡም። ታደሰ ኰስትሬ ከነዚህ ዓይነት
ጠማማውና ቅሌታሙ ነው።
ታደሰ ኰስትሬ እንደ ጠላ ቂጣ ከዚህ ከዚያ እየነኰርክ ከመገለባበጥና ከመለፍለፍህ በፊት አገርና ሕዝብን
ጠንቅቀህ እወቅ ተረዳ።አንተ እድሜህ ገፋ እንጂ ያወቅህው የለም።በተለይ በስዊድን አገር የሰው ልጅ
ክብርና ሰብዕዊ መብት፣የህግ የበላይነት በሚከበርበትና እንዲሁም ጀግና የኢትዮጵያ ልጆች በአሉበት
ተቀምጠህ አንተ ለከርስህ ለወያኔ ባንዳ አጋሚዶዎች ማቅራራት አትችልም።እስከሚያቅለሸልሽህ ልንገርህ።
ውድቀትህ በምድርም_ በሰማይም ሲዖል ነው። ብትሰነብት የወያኔ ከበሮ እስከሚቀደድ ነው። ያ ደግሞ
እጅግ ቅርብ ነው።በአንተና በወያኔ ጌታህ ጠባብ ዘረኝነትና ዘረፋ ምክንያት በግፍ ከኑሮው፣ከቤቱ
የተፈናቀለው፣ንብረቱን የተቀማው ሕዝብ በቅርቡ በሬሳችሁ ላይ ቆሞ የመንግሥት ሥልጣንና የአገሩ
ባለቤት ሆኖ እንደ መስከረም አበባ ያብባል።አንተ ግን በሰፈርከው ቁና ትሰፈርና በጋለ ምጣድ ላይ
ትንገረገባለህ። ይህን እወቅ ! ያን ጊዜ የገዛ ዘመዶችህ፣ጓዴኞችህ ሁሉም አሳልፈው ይሰጡህና ትበላለህ።
ታደሰ ወያኔ አፍቃሪ ሆነህ ለሆድህ የምታደርገው ቅሌት አገር ወገን ላይ ክህት ነው፣ የሚያጠፋህ ስህተት፣
ባለቤት እንደሌለው ቀላዋጭ ውሻ በአገኘበት እንደ የሚጮህ፣ ቀላል አንቱ የማትባል ሽማግሌ ሆነህ፣ ሥነ
ምግባር የጎደለህ ገልቱ፣ ገንዘብ አፍቃሪ፣ የወያኔ ባላንባራስ ነኝ ብለህ አመድ ቅማ እንደጠገበች አህያ
የምታናፋው የወኔ ባንዳ ከሃድዎችን ተማምነህ ነው።የነሱ ጊዜ ደግሞ አልቋል፣ አመድ ይሆናሉ።
ስለዚህ ስማ ! መቼም ደንቆሮ ነህ፣ ኢትዮጵያኖችን መተቸትና ማንጓጠጥ ትተህ አፍህን ማበሱና ቤትህን
ዘግተህ መቀመጡ የሚጠቅም በጐ አቋም መሆኑን አስብ። በጊዜ ንስሃ ገብተህ አቋምህን ከአገር ጋር
አስተካክለህ ብትቆም ይበጅሃል። አይ ! እኔ አውቃለሁ ማን ነክቶኝ የምትል ከሆነ ያው በአፍ ይጠፉ
በለፈለፉ ይከተላል።
በአገር፣ በሕዝብና በሰንደቃለማ ቀልድ የለም ትዕግስታችን አልቋልና አንተንም ከዚያው ከወገንከው ጋር
አስገብተን አብረን እንደ ጭቃ እናቦካና እናሸሃለን እንጂ ዘንድሮስ አንላቀቅም። ያልተገረዘ ምላስህ
እንዲሰቀጥጥ አስፈላጊው ትምህርት ይሰጥሃል።
ባንዳ ይጠፋል ! ! !
በአገር ክህደት የተሰለፉ ሁሉ ይወድማሉ ! ! !
ምንጊዜም ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል ! ! !
No comments:
Post a Comment