ሂውማን ራይትስ ዎችን ጨምሮ በርካታ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ረገጣና አፈና ተባብሶ መቀጠሉን ገልፀዋል። ሁሉንም የፓርላማ ወንበሮች በብቸኝነት ተቆጣጥሮ የሚገኘው ገዢው የኢህአዴግ መንግስት፣ የዜጎችን ሃሳብን የመግለጽ መብት ከማስፋፋቱ በተጨማሪ በነጻ የመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚወስደው እርምጃ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ድርጅቱ አመልክቷል። ከትናንት በስቲያ ሰኞ የተካሄደውን የሰብዓዊ መብት መድረክ ያዘጋጀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን በተለያዩ ጊዜያት በኢትዮጵያ ስላለው የሰብኣዊ መብት አያያዝ ስጋቶችን ሲገልፅ መቆየቱ ይታወሳል። በጄኔብ በተካሄደው በዚሁ ልዩ መድረክ የተሳተፉ በርካታ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ወቅታዊ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ረፖርት ማቅረባቸውንም በመድረኩ የተሳተፉ አካላት ገልፅዋል።
የእንግሊዝ የፓርላማ አባላትን ጨምሮ በርካታ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጀቶች ኮሚሽኑ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አያያዝን ጨምሮ በተለያዩ የፖለቲካ እስረኞች ላይ ክትትልን እንዲያደርግ ጥያቄ አቅርበው እንደሚገኙም ተችሏል። የኢትዮጵያ መንግስት ተወካዮች መድረኩን ረግጠው ስለወጡበት ምክንያት የሰጡት ምላሽ የለም።
- See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/10556#sthash.LOjgAnRQ.dpuf
No comments:
Post a Comment