Tuesday, October 6, 2015

የኃይለማርያም ካቤኔ አባላት ታወቁ * ሬድዋን ወደ ወጣቶች እና ስፖርት ሚ/ር ተገፉ * ሶፍያን አህመድ ተሰናበቱ * ሕወሓት አሁንም የአንበሳውን ድርሻ ይዟል -

Hailemariamየሕዝብ ተወካዮች የሌሉበት የኢህ አዴግ ፓርላማ ዛሬ ተሰብስቦ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ያቀረቡትን የካቢኔ አባላት አጸደቀ:: በዚህ ካቢኔ ውስጥ አሁንም ሕወሓት ዋና ዋና የስልጣን ቦታዎችን ይዟል:: የውጭ ጉዳይ ሚኒስተርነቱ; ኢኮኖሚው በሕወሓት ስር እንዲቆይ ሲደረግ አሁን ደግሞ በተጨማሪም አቶ ሬድዋን ሁሴን ይመሩት የነበረውን የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ቦታም ወስዷል:: በዚህም ቦታ ላይ የሕወሓቶ አቶ ጌታቸው ረዳ ተሹመዋል:: ለረዥም ጊዜ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ሁነው ሲሰሩ የቆዩት አቶ ሶፍያን አህመድ በአቶ አብዱላዚዝ መሀመድ ተተክተዋል:የሕወሓቱን የካዛንቺሱን መንግስት የሚላላኩት የካቤኔ አባላቱ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል:: አቶ ደመቀ መኮንን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል – በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ወይዘሮ አስቴር ማሞ – በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ – የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃን – የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው አምባዬ – የፍትህ ሚኒስትር አቶ አብዱላዚዝ መሀመድ – የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አቶ ተፈራ ደርበው – የእርሻ እና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሚኒስትር አቶ ስለሺ ጌታሁን
– የእንሰሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር አቶ አህመድ አብተው – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ ያዕቆብ ያላ – የንግድ ሚኒስትር አቶ አብይ አህመድ – የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ – የትራንስፖርት ሚኒስትር አቶ ሙኩሪያ ሀይሌ – የከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስትር ዶክተር አምባቸው መኮንን – የኮንስትራክሽን ሚኒስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ – የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ – የትምህርት ሚኒስትር አቶ ቶሎሳ ሻጊ – የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ – የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ – የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ – የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ -የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም – የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን – የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ደሚቱ ሀምቢሳ – የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚኒስትር ማዕረግ የካቢኒ አባል የሆኑ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሹመትን ለምክር ቤቱ አቅርበው አስፀድቀዋል። በዚህም መሰረት አቶ በከር ሻሌ – የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር አቶ ጌታቸው ረዳ – የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ – የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ዶክተር ይናገር ደሴ – የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል። - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47173#sthash.vEpZsgV6.dpuf:

No comments:

Post a Comment