ከኦሮሞ በላይ ኢትዮጵያዊ የሆነ ማን ነው?
########################
በኢትዮጵያ ውስጥ ኦሮሞ ያረገጠው እና ያልኖረበት መሬት ይኖራልን?
የኦሮሞ ህዝብ ከየትኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ነው ተጋብቶና ተዋልዶ ዝምድና ያልፈጠረው? ኦሮሞን ከኢትዮጵያ እምብርት አውጥቶ መጤ ለማድረግ መሞከርስ አላዋቂነት አይደለምን?
ኦሮሞን ማን ነው!? እንዴት ባለ ማስረጃስ ነው!?………አንዴ ከኬኒያ ሌላ ጊዜ ደሞ ከማዳስካር እንደ መጣ ሊያስረዳን የሚችለው። ምን አልባት ይህ ታሪክ ተፅፎ ከሆነም………ነጭ ሆን ብሎ ፊት ለፊት በጦርነት ማሸነፍ ያልቻለውን……… ኢትዮጵያዊያንን ለማበጣበጥ የፃፈው የተንኮል ታሪክ ይመስለኛል።
የኦሮሞ ህዝብ እንደ ሌላው ህዝብ ኢትዮጵያን በመመስረት ረገድ ውድ ደሙን አፍስሷል፣ አጥንቱንም ከስክሷል። ይሁንና የበላይነትን ለማሳየትና አንዱ ንጉስ ሌላውን ንጉስ ለማስገበር ይደረግ የነበረውን የእርስ በርስ ጦርነት ትርጉም ለውጦ የኦሮሞ ህዝብ ወረራ እንደ ተፈፀመበት በማስመሰል ከሀገሩና ከወገኑ ለመለየት በአንዳንድ የኦሮሞ ሊሂቃን በኩል ደባ እየተሰራበት ይገኛል።
ይህንን ድብቅ ሴራ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ተፈፃሚ ለማድረግ……… በዋነኝነት በነጭ ፀሀፊያን የተፃፉ ታሪኮችን እንደ ትክክለኛ ማስረጃ በመውሰድ ይጠቀሙበታል። ነገር ግን………ኢትዮጵያዊ ዜግነት ባላቸው ስመ ጥር የታሪክ ተመራማሪዎችና ፀሐፊዎች……… የተፃፉና የሚነገሩ ታሪኮችን መስማትም ሆነ ማንበብ በፍፁም አይፈልጉም። ከዚያ ይልቅ ኦሮሞ የታሪክ ተመራማሪና ፀሀፊያንን "ነፍጠኛ"፣ "የድሮ ስርአት አቀንቃኝ" በማለት ይሰድባሉ፣ ይንቃሉ፣ ያገላሉ። ፍፁም በስልጣን ጥም የተቃጠለ ፍላጎታቸውን ለማርካት የማይፈበርኩት የውሸት ታሪክ የለም። በዚያ ምስኪን ህዝብ ላይ ለመንገስ ጨርሶ እንቅልፍ የላቸውም። ከኦሮሞ በላይ ኢትዮጵያዊ እንደ ሌለ ለመናገር ሞራል የላቸውም። የስልጣን እና የሃብት ጥማቸውን ለማስተንፈስ የማይቆፍሩት የጥላቻ ጉድጓድ፣ የማይፈነቅሉት የቂም ድንጋይ የለም።
የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆ እንድትኖር ትልቅ ሚና ነበረው አሁንም አለው። ያለ ኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያን ማሰብ ከንቱ ድካም ነወ። በደም ከተሳሰረው ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ለመለየት ማሰብም ፍፁም የቁም ቅዠት ነው። በላቡና በደሙ ከሰራት ኢትዮጵያ ሀገሩ ለመለየት ማሰብ ቅዠት ብቻ ሳይሆን እብደትም ነው።
የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያዊ እንጂ ከሌላ ሐገር የመጣ መጤም አይደለም። ከኦሮሞ ህዝብ በላይ ኢትዮጵያዊ ሊሆን የሚችልም አይኖርም። ምክንያት:— በአፄ ቴዎድሮስ እና በአፄ ዩሐንስ የኦሮሞን ባላባቶችንና ህዝብ ባለ ማሳተፉ ምክንያት ያልተሳካው የሐገረ ኢትዮጵያ ምስረታ የኦሮሞ ባላባቶች ከእምዪ አፄ ምኒልክ ጋር በመሆንና ህዝቡን በማስተባበር የዛሬይቷን የታፈረችና ነፃ የሆነች ኢትዮጵያን ለመመስረት ተችሏል። ስለዚህ ነው የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያዊ ነው የምንለው።
No comments:
Post a Comment