Saturday, July 16, 2016

ቤታቸው-የፈረሰባቸው፣“የመንግስት-ያለህ”-እያሉ-ነው በቅርቡ በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ‹ማንጎ› በተባለው አካባቢ ቤታቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች “መውደቂያ፣ መድረሻ አጥተናል፤ ጫካ ውስጥ ከአውሬ ጋር እየተጋፋን ለመኖር ተገድደናል” ሲሉ እያማረሩ ይገኛሉ፡፡


 እስካሁን የት ናችሁ ብሎ ያነጋገራቸው
የመንግስት አካል እንደሌለና አስታዋሽ አጥተው እንደተጣሉ እኚሁ ተፈናቃዮች ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ ከነልጆቻቸው በክረምት
ዝናብና ጭቃ ሜዳ ላይ ወድቀው እየተሰቃዩ መሆኑን በምሬት የሚያስረዱት አባወራና እማወራዎቹ፤መንግስት የኤርትራ ስደተኞችን እንኳን
ካምፕ አዘጋጅቶ እየተቀበለ መሆኑን ጠቁመው ለዜጎቹ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ተማጽነዋል፡፡ ቤታቸው ፈርሶ በማንጎ ጫካ ከተጠለሉ
ነዋሪዎች ሶስቱ ስለቀድሞ አሰፋፈራቸውና አሁን ስላሉበት አስከፊ ሁኔታ እንደሚከተለው ገልጸዋል፡፡ “የመንግስት ያለህ!” እያሉም ነው፡፡
“የሚደርስልን አካል ካለ ይድረስልን!”
(አዛውንቱ ሃጂ አብደላ ሁሴን ቤታቸው ከፈረሰባቸው አንዱ ናቸው፡፡ እርጅና የተጫናቸው ሃጂ አብደላ እንባቸውን እያፈሰሱ ያሉበትን ሁኔታ ተናግረዋል፡፡)
“---ይፈርሳል ተብለው ቀደም ሲል ተነግሯቸው ሲከራከሩ የነበሩት ቀርሳ ኮንቶማና ኤርቶ ሞጆ የሚባል አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች እንጂ እኛ የማንጎ አካባቢ ነዋሪዎች ይፈርሳል ተብለን አናውቅም፡፡ የነሱን ነበር እየሠማን የነበረው፡፡ እነሱ አመት ከመንፈቅ በዚህ ጉዳይ ሲከራከሩ ነበር፤ ነገር ግን ቤታችን ከመፍረሱ አንድ ሁለት ቀን በፊት የእናንተም ሰፈር ይፈርሳል የሚል ነገር በሰፈሩ ላሉት የኢህአዴግ አባሎች በሚስጥር ተነገራቸው፡፡ እነዚህም ሚስጢረኞች ለአንዳንድ ሰው ነገሩን፤ በነጋታው ስብሰባ ወጣን፡፡ ከዚያ በፊት የመኖሪያ አካባቢ ነው ተብለን ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ዓመት የኖርንበት ቦታ ነው፡፡ መብራት አስገቡ ተባልን፣ መንገድ ስሩ ተባልን፣ ዘመናዊ የፖሊስ ጣቢያ ስሩ ተባልን፤ በአጠቃላይ የመኖሪያ ቦታ ነው አትስጉ አይነሳም ስንባል ነው የኖርነው፡፡ እንዴት እንዲህ ያደርጉናል ስንል ስብሰባ ወጣን፡፡ ኧረ የሚመለከተውን ጥሩልን ያወያዩን ስንል ለፖሊሶች አመለከትን፡፡ ፖሊሶች የወረዳውን አስተዳደር ጠሩልን፡፡ መጥተው “እውነት ነው የሚባለው?” ብለን ስንጠይቀው፤ “አዎ! እናፀዳዋለን ትጠረጋላችሁ” አለን፡፡ “እንዴ! ቆሻሻ ነው የሚፀዳው፤ እንዴት እንዲህ ትላላችሁ?; ስንል “የራሳችሁ ጉዳይ ነው” አለን፡፡ 

No comments:

Post a Comment