


በተመሳሳይ ደግሞ ተቃውሞ በአርጆ በኢሉባቦር ዞን በሬ ወረዳ በቢሶ ቀበሌ ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን በወያኔ አገዛዝ ሲጨቆን የነበረው ህዝብ ዳውን ዳውን ወያኔ እያለ የተቃሞ ሰልፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

እንዲሁም በጫንጮ ዛሬም የህዝባዊ አመፁ ተቀጣጥሎ ውሏል ፡፡ ዋሊያ ቢራ ተሸክሞ ሲጓዘወ የነበር ከባድ የጭነት መከና ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል በተለያዩ የኦሮሚያ አካባዎች የወያኔ ስርአትን በመቃወም የተለያዩ ተቃሞዎች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡በምስራቅ ወለጋና ጅማ አርጆ ወረዳ ኑኑ ቁምባ በተባለ ቦታ ተቃውሞ ሲደረግ መዋሉ ታውቋል ፡፡
በሰላሌ ቄሮዎችና የክልሉ ፖሊስ በጋራ በመሆን ስርአቱን በመቃወም የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና አገዛዙ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል በቃን በማለት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂዷል ፡፡ በኩዩም ከፍተኛ ተውሞ ተነስቶ በርካታ የስርዓቱ መገልገያ የሆኑ ተሸከርካሪ መኪናዎች መቃጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
No comments:
Post a Comment