
መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ የቀድሞው የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን) ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስጎደም ለ14 ዓመታት የነበሩበትን ድርጅት ከድተው ለኢህአዴግ ባለስልጣናት እጃውን መስጠታቸውን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ እየሰራ ያለው የቅስቀሳ ስራ በህዝብ ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው። የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ትህዴን የአርበኞች ግንቦት7 አንድ የጦር ክፍል እንደሆነ አድርገው ማቅረባቸው፣ እንዲሁም ውስጥ ለውስጥ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተያዘ፣ ድርጅቱ ፈረሰ እያሉ ማስራታቸው ብዥታ እንደፈጠረባቸው አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። መብራት በተደጋጋሚ መጥፋቱ ኢሳትን ለመከታታል እንዳላስቻለው የሚገልጹ አስተያየት ሰጪዎችም ፣ ትክክለኛውን መረጃ እንድናካፍላቸው ጥያቄ አቅርበዋል። አ
ንድ አስተያየት ሰጪ የአቶ ሞላ በጊዜ መክዳት ለትግሉ የሚጠቅም መሆኑን ተናግረው ፣ አሁንም የማጥራቱ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል
No comments:
Post a Comment