በቅርቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም እና አምባሳደር ግርማ ብሩ በዩናይትድ ሰቴትስ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው የቪኦኤ ሬዲዮ ጣቢያ በሌሊት በድብቅ በመግባት ሕጋዊ ስልጣኑ ሳይኖራቸው ስለስርጭቱ ለጥቂት የድርጅቱ ሠራተኞች የኢዲቶሪያል መመሪያ ከሰጡ በኋላ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት (ቪኦኤ) እና በህወሀት የበላይነት በሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት መካከል ያለው የሻከረ ግንኙነት ያልተጠበቀ አቅጣጫ ይዟል፡፡ ስብሰባው በሚስጥር በተካሄደበት ጊዜ የአምባገነኑ አገዛዝ ባለስልጣኖች ለሬዲዮ ስርጭቱ ሰራተኞች ስለዜና አዘጋገብ፣ እንደዚሁም ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ስለሚተላለፈው የስርጭት ጥራት ሁኔታ መመሪያ የመስጠት ሙከራ ያደረጉ ለመሆናቸው ከታመኑ ምንጮች በተገኙ መረጃዎች ተረጋግጧል፡፡
ከቪኦኤ ባለስልጣኖች ዕውቅና ውጭ በሚስጥር እንዲከናወን የተደረገው ይህ ስብሰባ የተካሄደው በዋሽንግተን ዲ.ሲ 330 ኢንዲፔንደንስ አቬኑ በሚገኘው በቪኦኤ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል የኢዲቶሪያል የስብሰባ ቢሮ ውስጥ ነው፡፡ ይህ ድብቅ ስብሰባ እንዲካሄድ የተደረገው ባልተለመደ እና እንግዳ በሆነ መልኩ በሰንበት፣ እ.ኤ.አ መስከረም 26 ቅዳሜ ዕለት ከስራ ሰዓት ውጭ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ ነበር፡፡ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ፕሮግራም ስርጭት ባልደረባ በሆነው በሰለሞን አባተ ግንባር ቀደም አደራጅ እና አስተባባሪነት እንዲሁም በአሜሪካ ድምጽ የትግርኛው ፕሮግራም ስርጭት ባልደረባ በሆነው በበትረ ስልጣን ተባባሪነት በዲፕሎማቶቹን እና ሁለት ቴክኒሸኖችን ጨምሮ ሰባት የቪኦኤ የስራ ባልደረቦችን ባካተተው ቡድን መካከል የተካሄደው ስብሰባ ተገቢነት የሌለው እና አግባብ ያልሆነ ተብሎ ተፈርጇል፡፡ አገዛዙ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ጠንካራ ትችት የሚያቀርቡትን ብዙሀን መገናኛዎች ጸጥ ለማድረግ እና የስርጭት አድማሳቸውን ለመገደብ እያራመደ ካለው አውን ያወጣ ስልት አንጻር ከፍተኛ በሆኑ የአምባገነኑ አገዛዝ ባለስልጣኖች እንደዚህ ያለ ስብሰባ መካሄዱ እና ስለቪኦኤ እያራገቡት ያለው የጥላቻ አጀንዳ በሕጋዊ መልኩ ስልጣን የተሰጠውን የመተዳደሪያ ደንብ እና የጋዜጠኝነት ስነምግባርን የሚጥስ ዕኩይ ድርጊት እንደሆነ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ይህ በቅሌት የታጀበ ስብሰባ እንዲካሄድ የተፈለገበት ዋናው ምክንያት አገዛዙን በየዓመቱ የፕሬስ ነጻነትን በመደፍጠጥ የቀዳሚነቱን ቦታ ከሚይዙት የፕሬስ ደፍጣጮች መካከል እያስመደበው የመጣ ስለሆነ ይህንን ሁነት ለማደብዘዝ ሲባል በጋዜጠኞች እና በጨቋኙ መንግስት መካከል መተማመን እና ትብብር እንዲኖር ለማድረግ ከመፈለግ የመነጨ ክስተት ነው፡፡ በስብሰባው ወቅት በተደረገው ንግግር የህወሀት ተወካይ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገውን የሬዲዮ ስርጭት ጥያቄ በማቅረብ እና በድብቅ የማስፈራሪያ ድርጊቶችን በመፈጸም በስርጭቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ መፍጠር እና የስርጭቱንም ይዘት ማስቀየር እንደሚቻል የቀረበውን ሀሳብ ለደህንነታቸው ሲባል አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው ይፋ አድርገዋል፡፡ እየተካሄደ የነበረው ስብሰባ ውይይት በመቅረጸ ድምጽ እንዳይቀዳ እግድ የጣለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በማያያዝም ቪኦኤ ጠንካራ የሆኑ ትችቶችን ለሚያቀርቡት የአየር ጊዜ በመስጠት እና ዓላማቸውን በኃይል ለማስፈጸም የሚንቀሳቀሱትን አመጸኞች ግንቦት ሰባትን ጨምሮ መንግስትን ለመገልበጥ ለሚደረገው እንቅስቃሴ ድጋፍ ያደርጋሉ በማለት ቅሬታውን አሰምቷል፡፡ ሚኒስትሩ በመቀጠልም ቪኦኤ “አሉታዊ ትረካ” ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰራ ሜዲያ ነው በማለት ቅሬታውን ገልጿል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47894#sthash.xlsbxP2c.dpuf
No comments:
Post a Comment