* "የፀጥታ አስከባሪዎች በሙሉ በአንድ ዕዝ ሥር ገብተው ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሆን ተደርጓል:: ከነገ ጀምሮ ለአንድ ወር ሰልፍ እና ከቤት ውጪ የሚደረግ ሕዝባዊ ስብሰባ የተከለከለ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳወቅ እወዳለሁ::ይህንን መመሪያ ተላልፎ በሚገኝ ክፍል ላይ የፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ጥብቅ እርምጃ እንዲወስዱ መመሪያ ተላልፏል::"
መለስ ዜናዊ የምርጫ 1997 ውጤት በተገቢው ሰዓት ይፋ አለመደረጉን ተከትሎ ሊነሳ ይችላል ብለው ለሰጉት ሕዝባዊ ተቃውሞ ቅድመ ማስጠንቀቂያ የሰጡበት ንግግር ነው::
በዚህ ማጠንቀቂያ መሠረት መጀምመሪያ በሰኔ ወር 97 ዓ.ም ፣ ቀጥሎ ጥቅምት 22 1998 ዓ.ም ንፁሐን ዜጎች በአደባባይ ተገድለዋል። ዛሬ የጥቅምቱን ግድያ 10ኛ ዓመት እናስባለን::
* በባህርዳር የባጃጅ ታክሲ ሾፌሮች አደማ ቀጥሏል። አድማውን አስተባብረዋል የተባሉ ሰዎች እየታሰሩ ነው። የመንግስት ታጣቂዎች በከተማው ተበትነዋል።
* የአርበኞች ግንቦት 7 ትግልን የሚያወድስ እና "ኢህአዴግ ይውደም" የሚል በራሪ ወረቀት በአርባምንጭ ከተማ መበተኑን ተከትሎ በነዋሪው ላይ የእስር እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
በ1959 የተመሠረተው ታሪካዊው በላይ ተክሉ ኬክ ቤት ሊፈርስ ነው።
ልማት ማለት ባለሞያዎችን አያማክርም ወይ፣ ቅርሶችን እና ታሪካዊ ቦታዎቻችንን እንዴት እንጠብቃለን? ለሚሉ ጥያቄዎች የሥነ ምህንድስና ባለሞያ አነጋግረናል።
*ከኬንያ የሚታገቱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ጨምሯል። የህወሓት ደህንነት ክፍል ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል ሥርዓቱን ይቃወማሉ የሚላቸውን ሰዎች በሽብርተኛነት በመፈረጅ አፍኖ እየወሰደ ነው። ይህንን በመቃወም ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ኬንያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ኢትዮጵያዊያን ሠልፍ አድርገዋል። ኤምባሲውም በጉዳዩ ላይ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ቃል ገብቷል።
ኢሳትን አድምጡ
No comments:
Post a Comment