
በአክሱም ስታዲየም የአክሱም ከተማ እና የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታ እየደረገ ባለበት ወቅት ደጋፊዎች ባነሱት ሁከት የተነሳ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ ስታዲየሙ ሄልሜት ባጠለቁ ልዩ ኃይሎች መከበቡ ታውቋል::
በኢትዮጵያ ከፍተኛው ሊግ የሚጫወቱት ሁለቱ የትግራይ ክልል ክለቦች ደጋፊዎች ያነሱት ሁከት ላይ ተጫዋቾች ሳይቀሩ መፈንከታቸውና ደጋፊዎች በድንጋይ ሲከታከቱ እንደቆዩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::
ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም የቡና ደጋፊዎች ባነሱት ብጥብጥ ስታዲየሙ ላይ እና በሰዎች ላይ ጉዳት ከመድረሱም በላይ አንድ ሰው መሞቱን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም
::




No comments:
Post a Comment