Tuesday, July 12, 2016

ፋሽስቱ ሕወሓት የጎንደር ዐማሮችን ለመጨፍጨፍ በንጹኃን ሰዎች ላይ የጥይት እሩምታ ከፍቷል፡፡


Muluken Tesfaw ማኅበራዊ ሚዲያን ዘግቶ የጎንደር ዐማሮችን ለመጨፍጨፍ በንጹኃን ሰዎች ላይ የጥይት እሩምታ ከፍቷል፡፡ ከፊል የወልቃይት የዐማራ ማንነት አስተባባሪ ከሚቴዎችን አፍኖ ወስዷል፤ ቀሪዎችን ለመውሰድ በመከላከያና በፌደራል ፖሊስ አካባቢው ከቧል፡፡ አንድ የወልቃይት ዐማራ በጥይት ተመቶ ሆስፒታል ገብቷል፡፡ ዛሬም እንደ ትናንቱ በየአደባባዩ ያፈሰሱት ደም ቆሌያቸውን የሚያረካው አልሆነም፡፡
ሞት ለዐማራ ሕዝብ አዲስ አይደለም፤ የፋሽስቱ የሕወሓት ትግሬ መንግሥት ሃያ አምስት ዓመት ሲገድለው ኖሯል፡፡ የዐማራ ሕዝብ ለሁሉም እየኖረ ብቻውን ሲሞት ነው ታሪክ የሚያውቀው፡፡ የጎንደር ዐማሮችም የወልቃይት ዐማራ የማንነት ኮሚቴዎችን (ያልተወሰዱትን) አሳልፈው እንደማይሰጧቸው አምናለሁ፡፡ እርግጥ ነው ወያኔዎች ብዙ ሰው ይገድላሉ፤ መቼስ ያልገደሉበት ጊዜ አለና፡፡
የወልቃይትን ዐማሮች በተወለዱበት ቀየ፣ ባባቶቻቸው ርስት እነርሱ መጥተው አባረሯቸው፡፡ ቀያቸውን ለቀው ጎንደር ከተማ ባሉበት ‹‹እስኪ የሚያድናችሁን አያለሁ›› እያሉ በየተጠጉበት መንጥሮ መውሰድ የደረሱበትን የእብሪትና መታበይ መጠን ያሳያል፡፡
ይህ የአንድ አናሳ ቡድን ፋሽስታዊ ሥርዓት በዐማራው ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን በደል ዘርዝረን አንዘልቀውም፡፡ በጎንደር ከተማ ብቻ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ የገደለውን ሰው ብዛት ማንም ቆጥሮ አይዘልቀውም፡፡ ይህ ሥርዓት በ85/86 ዓ.ም. በአዲስ ዓመት ዋዜማ አደባባይ ኢየሱስ ገብቶ ከ60 በላይ ምዕመንን ረፈረፈ፤ የቤተ መቅደስ መጋረጃዎች በደም የጨቀየ የቤተ መቅደስ መወልወያ ሆነ፡፡ የሞተ አስከሬን የከፈን ጨርቅ ሆነ፡፡ በ2006/7 ዓ.ም. ጥረው ግረው የሠሩትን ቤት በገንፎ ቁጭ አካባቢ አፈራረሰ፤ ብዙ ሰዎችንም በጠራራ ፀሐይ ገደለ፡፡ በ2008 ዓ.ም. ማረሚያ ቤት አቃጥሎ በሕግ ጥላ ሥር ያሉ ከ100 የሚልቁ ዐማሮችን በጅምላ ጨረሰ፡፡
ማሳሰቢያ፡ በአካባቢው ያላችሁ ዐማሮች መረጃዎችን በመለዋወጥ እንድትተባበሩ አሳስባለሁ፤ ገለልተኛ ነን የሚሉ የመገናኛ ብዙሃን ጉዳዩን ይከታተሉት ዘንድም እጠይቃለሁ፡፡ 
Source Muluken Tesfaw - ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment