ብአዴን የቀድሞው ኢሕድን የህውሃት አማርኛ ተናጋሪ ክንፍ መሆኑን፤ ትምክተኛ፣ የቀድሞ ስርዓት ናፋቂ፣ ፀረ-ትግሬ ተብሎ እየተነቀለ እየተለቀመ በግህነብ በመርዝ ያለቀው፣ በማዕከላዊ ጥፍሩ እየተነቀለ የሚመረመረው፣ ልብሱን አስወልቀው እርቃነ-ስጋው ላይ እየሸኑ 'ሽንታም አማራ' ብለው የሚሰድቡት ወንጀል ሰርቶ ሳይሆን አማራ በመሆኑ ብቻ መሆኑን ለእናንተ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብኛል።
አንተም፣ ሽንታም የተባለውም፣ ጥፍሩ የተነቀለውም፣ በግህነብ የተገደለውም፣ እኔም አማራ ነን። አማራ ብለን የምንጮኸው የአማራን የበላይነት ለማምጣት ወይም ህወሃቶቹ፣ ተከታዮቻቸውና ወዳጆቻቸው እንደሚሉት የአማራን የበላይነት ማስጠበቅ ሳይሆን አማራን ከመጥፋት ለመታደግ ነው።
ላለፉት 25 አመታትም ዛሬም በስልጣን ላይ ያለው ህወሃት ሲመሰረትም አሁንም አማራን በጠላትነት የፈረጀው በሌሎችም ያስፈረጀው፣ ከይዞታው የነቀለው ያስነቀለው፣ የገደለውና ያስገደለው ነው። ትናንት እነ አቶ አታላይ ዛፌን ተነጥቀናል፣ ከዚያ በፊት እነ ፕሮፈሰር አስራት ወልደየስን አጥተናል። ባለፈው አመት ወጣቱ የህግ ጠበቃ ሳሙኤል አወቀ ተገድሎል። እነ አንዷለም አራጌ እድሜ ልክ ተፈርዶባቸው ቃሊቲ ተዘግቶባቸዋል። እነ አግባው ሰጠኝ በሞትና በህይወት መሀል ሆነው በቄሌንጦ ጨለማ ክፍል ተቆልፎባቸዋል። በመቶዎች ሳይሆን በሺዎችና አስር ሺዎች በግህነብና በሌሎች በሚታወቁና በማይታወቁ እስር ቤቶች አማራ ስለሆኑ ብቻ ታስረው በፈጠራ ውንጀላ እየማቀቁ ነው።
ከዚህ በላይ የምንጨምረው ግን አይኖርም። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴን አሳልፎ ለህወሃት መስጠት በራስ ላይ ሞት መፍረድ ነው። ኮለኔሉን መጠበቅና ከነፍሰ-ገዳዮች መከላከል የሁሉም ሀላፊነትና ግዴታ ነው። ኮለኔሉ የተነሱት አማራን ከመጥፋት ለመታደግ ነውና።
ግልባጭ፤
ለመከላከያ ሠራዊት የአማራ ተወላጆች
ለፌደራል ፖሊስ የአማራ ተወላጆች
ለፀጥታና ደህነት መ/ቤት የአማራ ተወላጆች
ለብአዴን አባሎች
ለአማራው ህዝብ
No comments:
Post a Comment