Friday, July 15, 2016

የጎንደር ህዝብ እየተዋደቀ ያለው ለአንጡራ ሀብቱ ነው። ለቤተሰብ ፣ ልጅ እና ሚስቱ ነው።ወሮበሎች የወልቃይት መሬት የኛ ነው ፣ ሁመራ አብደራፊ የኛ ነው ሲሉ ፣ የአባት ቅድመ አያቱ ባድማ ላይ ለዘመናት የኖረን ህዝብ ንብረቱን ለመንጠቅ ነው። በኢትዮጵያ ህዝቦች ደካማ ጉልበት ሀብት ያካበተው ቀማኛ ቡድን ፣ በግፍ የሰበሰበውን ንብረት ይበልጡኑ ለማካበት የፈጠራ ችሎታ እንደሌለው ደግሞ እና ደጋግሞ አሳይቷል። ቀላል ሆኖ ያገኙው ነገር ቢኖር የሌላ ሰው ንብረት የሆነውን መሬት በጉልበት መንጠቅ ነው። በድብቅ ሌብነት እና በግልፅ ዝርፊያ ከተከማቸ ገንዘብ ፍርፋሪ የሚወረወርለት የትግራይ ህዝብም ለወሮበሎች እስከዛሬ ድረስ ሲሰጥ የቆየውን ጭፍን ድጋፍ ለከት ቢሰራለት ሳይሻል አይቀርም እንላለን።ትግራውያን ለፍታችሁ እና ደክማችሁ አገራችሁን አሳድጉ። ይህ መልሶ ማቋቋም የሚለው ማጭበርበር ከእንግዲህ ቦታ የለውም። የትኛው ግብርና ፣ የትኛው ኢንዱስትሪ ፈረሰባችሁ እና ነው መልሶ መተካት ያለበት? ኢትዮጵያውያንም ካሳ የሚከፍሏችሁ በማን እዳቸው ነው? ከትግራውያን በላይ ምን የተሻለ ኑሮ ኖረው ያውቃሉ? የትግራይ ህዝብ የተሻለ ኑሮን ለመመስረት እርዳታ ያስፈልገዋል ከተባለ ፣ ያ ምናልባት ትክክል ሊሆን ይችላል። ይህ በመመካከር እና በመነጋገር ሊሆን የሚችል ነገር ነው። በዚህ አሁን ጎንደር ላይ እየተከሰት ባለው አሳዛኝ ግጭት ልንማር የሚገባን ብዙ ነገር አለ ። ከሁሉም ነገር በላይ ግን የሚያሳየን ለግፍም መጠን እንዳለው ነው። ድሀው ህዝብ በቃ ብሏል። ጀሮ ያለው ይስማ። ዛሬ በጎንደር የተገረማችሁ ወሮበሎች ግን ፣ አድፍጠው የሚጠብቁ የጎጃም አንበሶችን አትርሱ።Mola Setarege - Yekubat Magado

No comments:

Post a Comment