Tuesday, July 12, 2016

ሰበር ዜና ከትናንት ምሽት ጀምሮ በጎንደር ከተማ በወያኔ ትግሬ እና በጎንደር ህዝብ መካከል ከፍተኛ የከተማ ዉስጥ ዉጊያ(urban warfare) እየተካሄደ ይገኛል ።

የዉጊያዉ መነሻ ወያኔ ስድስት የወልቃይትን የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላትን አስሮ ወደ አዲስአበባ ለማጓጓዝ ሲሞክር በከተማው ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃዉሞ እና ቁጣ በማስነሳቱ እንደሆነ ታውቋል። ጀግናው የጎንደር ህዝብ እስካፍንጫቸዉ ከታጠቁ የትግሬ ሰራዊት ጋር በባዶጁ እየተናነቀ ሲሆን እስካሁን ከሁለቱም ወገን ከ18 ሰዎች በላይ ተገለዋል።የክልሉን ህዝብ እጠብቃለሁ ያለው የዐማራ ፖሊስ ህዝቡን ለወያኔ ጥይት አስረክቦ ተሸሽጓል። በዉጊያዉ የወያኔትግሬ ንብረት የሆኑ አንድ የደህንነት ላንድ ክሩዘር መኪና አንድ ኦራል እና እንዲሁም ንብረትነቱ የህዉሓት የሆነዉ የሰላም ባስ በታጋይ የጎንደር ወጣቶች ጋይቷል። በአሁኑ ሰዓትም ወያኔ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ የሆነውን የኮለኔል ደመቀን መኖርያ ቤት በሞርታር እያፈራረሰ ሲሆን ህዝቡም ወያኔን ከቦ በራሱ አደረጃጀት በመፍጠር እያስጨነቀዉ ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከሰላማዊ ከተማነት ወደ ጦር አዉድማነት በተቀየረችዉ ጎንደር ዉስጥ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሂደት ተስተጓጉሏል። ወያኔ የማህበራዊ ድረገፆችን ያገደበት ምክንያት ዐማራውን ጨለማን ተገን አድርጎ ለመጨፍጨፍ እንደሆነ ገሃድ ወጥቷል። ዉጊያዉ በከተማው አጎራባች በሆኑት በማክሰኝት እና በዳባትም በፍጥነት እየተዛመተ ይገኛል።

No comments:

Post a Comment