ሰፌድና ወንፊት: እያለ በጃችን
ያልተነፋ ዱቄት: ምነው ማቡካታችን::
– አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ
ሚሊዮን ዘአማኑኤል
ሕወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የአገሪቱን ሁለተኛ የ እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ 2008-2012 እ.ኤ.አ ሲያወጡ የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን የሃያ ዓመት የኮንትራ ውል ማለቁንና ወደ ኢትዮጵያውያኖች ንብረትነት መሸጋገሩን ምንም ሳይሉን እንዳላወቀ ሆነው ለማለፍ ሞክረዋል:: የኢትዮጵያ ሕዝብና የክልሉ ሕዝብ ይሄን የሃገር ኃብት ከሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ሜድርክ ንብረት በህግ አስመልሶ የኢኮኖሚ ጥቅምና የውጭ ምንዛሬ ማግኛ ማድረግ የዜግነት ግዳጃችን ነው:: ሃገሪቱም በትንሹ በዓመት 500 ሚሊዮን ዶላር በወርቅ ማዕድን ሽያጭ ከውጭ ምንዛሪ ገቢ ታገኛለች:
:http://www.zehabesha.com/amharic/archives/63801
No comments:
Post a Comment