

ነገ ለታላቁ ቅዳሜ ሀምሌ 30/2008 የነጻነት ዋዜማ ሰልፍ የምንገናኘው መስቀል አደባባይ መሆኑ ታውቆ የጉዞ መስመራችን እንደሚከተለው ከዚህ በታች የተመለከተውን ይመስላል
———————
1. አስኮ፣ ቡራዩ አዲስ-ከተማና ጉለሌ በውንጌት በኩል፣
2. አየር ጤና፣ ካራ፣ ወለቴ፣ አለምገናና ልደታ በጦር ሀይሎች በኩል፣
3. ጀሞ፣ ለቡ፣ ላፍቶ፣, መከኒሳ፣ ቄራን ጨምሮ በሳርቤት በኩል፣
4. አቃቂ-ቃሊቲ፣ ሳሪስ አቦና ጎተራ፣
5. ቦሌ፣ ገርጂ፣ ሲኤምሲ፣ ሃያት፣ ጎሮና መገናኛ አንድ ላይ፣
6. ሽሮሜዳ፣ 6፣ 5ና 4 ኪሎ በአንድነት፣
7. ድል በር፣ አዲሱ ገበያ፣ ሰሜን ማዘጋጃና ሩፋዔል ፒያሳን ጨምሮ በአንድነት፣
8. ለገጣፎና ለገዳዲ፣ መሪ፣ ኮተቤ፣ ካራና የካ እንዲሁም ካዛንቺሶች በአንድነት በመሆን ከዚህ በላይ በተመለከተው አሰላለፍ ነገ በሰአታችን መስቀል አደባባይ የምንገናኝ ይሆናል፡፡
9. ገላንና ሰበታዎች ይፋዊ እቅዳችሁን በአስቸኳይ እንድታሳውቁን እናሳስባለን
10. ሱሉልታና ሆሎታዎች ብቻቸውን ለመውጣት ወስነዋል፡፡
==============
ማሳሰቢያ——–
አዲስ አበባ የሀገሪቱም ሆነ የኦሮሚያ እምብርት እንደመሆኗ የመስቀል አደባባዩ የነገ የነጻነት ዋዜማ ሰልፍ ወሳኝ መሆኑ አሌ የማይባል ከመሆኑም ባሻገር የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ልኡካኖች፣ አለማቀፍ ሚዲያዎችና ኢምባሲዎች እንዲሁም በአካባቢው ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ የአፍሪካ አንድነትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ ጽ/ቤቶች ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተሉ እንደሆነ በአንክሮ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የነጻነትና ባርነት እንዳንገሸገሸን የሚያሳዩ መፈክሮቻችንን ስርአት በጠበቀና በተናበበ አግባብ ማቅረቡ ለወሳኙ ድል የማይናቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ከግምት በማስገባት በዚሁ መሰረት መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል፡፡
የነገው ሰላማዊ የነጻነት ዋዜማ የተቃውሞ ሰልፍ በአፍሪካ በአይነቱ የአረብ ጸደይ/Spring እየተባለ ከሚታወቀው የአደባባይ የነጻነት ትግል ቀጥሎ የመጣ እጅግ ታላቅ ንቅናቄ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
#የጭቁኖች የተባበረ ክንድ ወያኔን ይደቁሳል!!
#ድል ለተጨቆኑ ህዝቦች በሙሉ
No comments:
Post a Comment