Wednesday, August 3, 2016

ሰዉ መሳይ በሸንጎ አንዳንዱ ሰዉ አደባባይ ላይ ሲታይ ሰዉ ይመስላል። ሸንጎ ላይ እዉነት ተናጋሪ ይመስላል። መድረክ ላይም ሀቀኛ ታማኝ እና ሚዛናዊ መስሎ ይቀርባል።


 የሚገርመው ወደ መድረክ ወጥቶ ከህዝብ ጋር ከመገናኘቱ ከሰዓታት በፊት በንፁሓን ላይ ያላግባብ ፈርዶ፣ ባለጉዳይ ጆሮ ላይ ስልክ ዘግቶ፣ በፅሐፊዋ አማካኝነት እያለ እንደሌለ አስነግሮ፣ መብታቸውን የጠየቁ ሰዎችን እንዲታሰሩ ትዛዝ ሰጥቶ፣ ሠራተኞች ማግኘት የሚገባቸዉን ጥቅማጥቅሞች ከልክሎ፣
ቅሬታ አቅራቢዎችን አሸማቆ በተዘጋጀለት መድረክ ላይ ሰዓቱን ጠብቆ ጉብ ይላል ። ከዛስ? ከዛማ መተርተር ይጀምራል።
ሌሊት ስለ ሰላም እና ስለ ልማት ሲያስብ እንቅልፍ እንዳልወሰደዉ፣ የዜጎች መሰረታዊ ጥያቄ እረፍት እንደነሳዉ፣ ፍትሐዊ ብይን መስጠት የሂወቱ መርህ እንደሆነ፣ ለሀብት እና ንብረት ግድ እንደሌለው፣ ለህዝቦች እንደሚደክም፣ እንደማያዳላ፣ ለባለጉዳዮች ጥልቅ ፍቅር እንዳለው፣ ቢሮዉ ሲመጡ አቅፎ የሚስም፣ እንደሆነ ይምላል ይገዘታል።
ካሳ ተክለብርሃን እንዲህ አይነት ሰዉ ነው። ይሄንን አፉ ማር ሰዉ በደንብ ማወቅ ከፈለጋችሁ የቀድሞው የህብር ስኳር መስራች እና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው ከኢሳት ጋር ያደረገዉን ቆይታ ተከታተሉት። ይሄን የምለው ካሳ ተክለብርሃን ቀና እና የተሻለ ነው ብላችሁ ለምታስቡ ሰዎች ነው። ይቆርጥላችኋል።
ስለዚህ ሰዉ ይችን እንድል ያስገደደኝ ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ዲያስፖራው ጋር በተደረገ ዉይይት ስለ ወልቃይት ጉዳይ ተጠይቀው በሰጠዉ ምላሽ ነው። ወልቃይት የትግራይ ነው ብሎ ደመደመ። ወልቃይት የትግራይ የሆነበትን ምክንያት ሲናገር ደሞ አብዛኛዉ ሰው ትግሬኛ ስለሚናገር ከትግራይ ህዝብ ጋር ቢኖር ይሻለዋል በሚል ሂሳብ እንደሆነ ጠቆመ ። ታድያ እንጥፍጣፊ ሚዛናዊነት ቢኖረዉ ኖሮ በህግ የተያዘን እና በሂደት ላይ ያለን ጉዳይ ባላሳረገዉ ነበር።
እዉነቱ ግን ኢህአዴግ በታሪኩ የሚፀፀትበ፣ ሀገሪቱን ወደማያባራ የእርስበርስ ጦርነት የምትቀየርበት ክስተት ወልቃይት መሆኗ ነው ። ይሄን ለማወቅ የሰሞኑን አካሄዶች ማየት በቂ ነው ። የአማራ ህዝብ ጦር አዉርድ ብሎ ወደላይ አያንጋጥጥም። ከወረደበት ግን መክቶ መልሶ ማደባየት ያዉቅበታል።
Esayas Tamiru

No comments:

Post a Comment