Sunday, August 14, 2016

የአማራ ተጋድሎ – የቀጥታ ዘገባ | Live Blog


በፈራረሱ ፎቆች ስር ሳይቀር በወሎ የሰፈሩት አልሞ ተኳሾች ፎቶ ደርሶናል

ይህ ገጽ በየሰዓቱ አዳዲስ መረጃዎች ሲገኙ ለናንተ መረጃዎችን እናደርስበታለን:: ስለሆነም ይመላለሱ::

የአማራ ክልል አስተዳደር በህወሓት እጅ ስር ወደቀ!
በባይነሳኝ ወልደማርያም

(ማምሻውን) በተገኘ ውስጣዊ መረጃ የአማራ ክልል አስተዳደር በትግራይ ህወሓት እጅ ስር ወድቋል። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከመደበኛ ስራቸው ተነስተዋል።
የአማራ ክልል ምክርቤት በአስቸኳይ ስብሰባው ገዱ አንዳርጋቸውን በይፋ ከስልጣን ያነሳል ተብሎ ይጠበቃል።
የአማራ ክልል አስተዳደር በ5 ኮማንድ ፖስቶች ተዋቅሯል።
1.ምዕራብ ጎጃም ኮማንድ ፖስት
2.ምስራቅ ጎጃም ኮማንድ ፖስት
3.ጎንደር ኮማንድ ፖስት
4.ወሎ ኮማንድ ፖስት
5.ባህርዳር ኮማንድ ፖስት

ምስራቅ ጎጃም ኮማንድ ፖስት በዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል ከደብረማርቆስ ይመራል። ምዕራብ ጎጃም ኮማንድ ፖስት በብናልፍ አንዷለም፤ ወሎ ኮማንድ ፖስት በአለምነው መኮንንና ገነት ዘውዴ ጥምረት፤ ጎንደር ኮማንድ ፖስት በተፈራ ደርበውና አይለኝ ሙሏለም ይታዘዛሉ። ተጨማሪ ኮማንድ ፖስት ሰሜን ሽዋ ላይ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል።
ሁሉም ኮማንድ ፖስቶች በአንድ እዝ ስር ሆነው በደመቀ መኮነን እገዛ በአባይ ፀሃዬ ይመራሉ። የአማራ ክልል ፀጥታና ደህንነት ቢሮ መሉ በሙሉ በህወሓት ማዕከላዊ የፖለቲካ አመራር ስር እንዲሆን ተወስኗል።
ወሎ
ሕዝብ በስልኮቹ ፎቶግራፎችን በማንሳትም በመታገል ላይ ነው:: ይህ የምታዩት ፎቶ የተነሳው በወሎ ክፍለሃገር ነው:: እነዚህ የትግራይ ነፃ አውጪ አልሞ ተኳሾች በፈራረሱ ህንፃዎች ስር ሁሉ ተደብቀዋል:: ሕዝብ ይያቸው:: የትግራይ ነጻ አውጪ አማራ መሬት ላይ ምን ይሠራል?

wello

መቄት – ወሎ
በሰሜን ወሎ ዞን ውስጥ የምትገኘውና ለጎንደር አዋሳኝ የሆነችው መቄት ከተማ ውስጥ ሕዝብ የልዩ ሚኒሻዎችን እና የአጋዚ ጦርን ሳይፈራ ሰልፍ ወጥቷል:: እንደሚሰማው ከሆነ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር በርካታ ሰልፈኞችን ቢያስርም ሰልፈኞቹ ግን 02 ቀበሌ ገረገራ ከሚባለው ወደ ፍላቂት 01 ቀበሌ እየመጡ ነው:: ሰሜን ወሎ ዞን ውጥረቱ አይሏል::
meket city
welo meket 2

መቄት – ወሎ
በወሎ መቄት ከተማ እየተደረገ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ፎቶግራፍ ደርሶናል:: በርካታ ሕዝብ ወጥቶ በመቄት ከተማ ተቃውሞውን እያሰማ ነው:: ሕዝቡ የሕወሓት መንግስት በቃን እያለ እይጮኸ ነው::
‪‎ማሻ‬ መቅደላ – ሙስሊም መሆን ወንጀል የሆነባት ከተማ
አብዱራህማን አህመድ ቢቢኤን:-
8/12/08 የዛሬውን የወሎ ተቃውሞን ተከትሎ ሰሞኑን በማሻ ከተማ ጠንከር ያለ ፍተሻ ሲደረግ እንደነበር ቢታወቅም ዘወትር እስልምናን ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱት የወረዳዋ ንውሶች ዛሬ በማለዳው በመነሳት በማሻ መናሃሪያ ፍተሻ በማካሄድ ወደደሴ ለመሄድ ጀለብያ ለብሰው የተገኙ ሙስሊሞችን ከመኪና አውረደው ፖሊስ ጣቢያ እንዳሰሯቸው ታውቋል።
dereje Habtewold
ደብረማርቆስ
አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት አብማ ቅድስት ማሪያም ካቴድራል ቤተክርስቲያን ምዕመናን እንዳይገቡ ተከለከሉ። ከተማዋ ውጥረት ውስጥ ናት። ምንም አይነት እንቅስቃሴ አይታይም። ነዋሪው ከቤቱ መውጣት አልቻለም። ጠቅላላ ወጣቱ ታፍሷል። እስር ቤቶች ሞልተው በርካታ የከተማው ኑዋሪ በጅምላ ንጉስ ተክለሃይማኖት ሁለተኛ ደረጃትምህርት ቤት ታጉሯል። የትራስፖርትም ሆነ ሌሎች የህዝብ አገልግሎቶች ተቋርጠዋል። ህዝቡን ስለፈሩት ሶስት ቀን ሙሉ ታንክ እየነዱ የከተማውን ህዝብ ሲያስፈራሩት ቆይተዋል::
ወልዲያ
weldiaወልዲያ የተወረረ ከተማ መስሏል:: ምንም አይነት የሚቀሳቀስ ነገር የለም:; ሱቆች ሁቴሎች እደተዘጉ ናቸው:: የመኪና እቅስቃሴ የለም:: በማይታወቁ ሚኒሻዎች እና በአጋዜ ወታደሮች ከተማው ተከቦ ነው ያለው:: አድኖ ተካ የተባለው ወድንድም ወልደያ ሆስፒታል በነርስ የሚሰራ ሲሆን የሕወሓት ተላላኪዎች ትናናን የት እንደወሰዱት አይታወቅም:: ጓድኞቹ እና ቤተሰቦቹ የት እንዳለ ቢጠይቁም ወልዲያ እንዳለ ቢነገራቸውም ሊያገኙት አልቻሉም::
ደብረብርሃን
ከስንታየሁ ቸኮል
ዛሬም ደብረ ማርቆስ አደገኛ ውጥረት ይታያል ሰው በቁጣ እየተሰባሰበ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ሸበልበረንታ ብቸና መፋጠጡ እንደቀጠለ ነው! ደብረ ብርሃን ወሬው በሙሉ የአማራ ሕዝብ ከደደቢት ወራሪ ጋር የጀመረው የጀግንነት ተጋድሎ አጋርነታቸውን ለማሳየት ሆኗል፡፡ ሞት የማያፈራ እሳት የጨበጠ የወሎ ወጣት አደባባዮን በተቃውሞ ሰልፍ ሊያጥለቀልቀው ከጫፍ ደርሷል፡፡ መጪው ጊዜ ለዘረኞች ጨለማ ሲሆን ጭቁን ሕዝብ በድል መንገድ ላይ ይገኛል!!
(ደብረብርሃን)

ሸዋሮቢት
ጀግናው የቀወት ወረዳ ህዝብ ሸዋሮቢት ከተማ ከፍትኛ የተሳካ ተቃውሞ በማለዳው ጅምሮታል ፣አድሚራሎቻችን የትግሉን አቅጣጫ ይቀይሩታል ። ይፋት እና ቀወት ወረዳበአንድነት የጀመሩት ትግል ወደ ምንጃር እንደሚያመራ ሚስጥራዊ የመረጃ ክፍላችን ገልጾአል ፣የወረዳ አስተዳዳሪዎች ፣ዛሬ ምሽት ላይ አፈና በሸዋሮቢት ከተማ ማሪያም ሰፈር በሚሰኘው ቦታ የሚገኘውን የወረዳ አስተዳደር ጥቃት ለማድረስ መዘጋጀቱን ሲጠቁም ፣ይህ ሊሆን የሚችለው በንጹሃን ዜጎች ላይ ክፉኛ ደም የፈሰሰ ከሆነ እነኢህን ሰዎች መሰዋእትነት ከማቅረብ ወደኋአላ አይባልም ሲል አድሚራል ተናግሯል

No comments:

Post a Comment