
የተረሸኑት ሁለቱ እስረኞች ማንነታቸውን ለማጣራት እየሞከሩ እንደሆነ የውስጥ ምንጮች የዘገቡ ሲሆን፤ ሟቾቹ የሕዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ኡስታዝ አህመዲን ጀበልና ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ባሉበት ክፍል ውስጥ የታሰሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሕዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ግን እስካሁን ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ለማወቅ ችያለሁ፡፡
መንግስት በቅርቡ በቃሊቲ ዞን 1 እና ዞን 2 ‹‹ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ታሳሪዎች ስም ዝርዝር›› በሚል ከ140 በላይ የሚሆኑ ታሳሪዎችን ስም ለጥፎ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ቀድሞውኑ ሊረሽናቸው ያሰባቸውን አካላት አሰናድቶ ያስቀመጠው መንግስት በአሁኑ ሰዓት በየእስርቤቱ ያለምንም ሃይ ባይና ከልካይ በማን አለብኝነት ዜጎቻችንን መረሸኑን ተያይዞታል፡፡
እነዚህ እጆቻቸው ባዶ የሆኑ፣ ያልታጠቁና በሕግ ስር የሚገኙ የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ታሳሪ ኢትዮጵያውያንን በጨለማ በመረሸን መንግስት እያደረገ ያለውን አረመኔያዊ ተግባር በአስቸኳይ ሊያቆም ይገባል፡፡ ወኪሎቻችን ላይ አንዲት እንኳ ችግር ቢደርስ ከችግሩ ጋር የተያያዙ አካላቶች በሙሉ ከሙስሊሙ ኢላማ ሊያመልጡ እንደማይችሉ አምባገነኑ መንግስት ማወቅ አለበት፡፡
"ድል ለተጨቆኑት በሙሉ"
No comments:
Post a Comment