Monday, May 22, 2017

የኢትዮጵያ አገር አድን ጉባኤ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ

ኑ !! የጋራችን ጉዳይ በሆነው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እንምከር !
በአሁን ወቅት አገራችን የገጠማት አገዛዝ ደግሞ ከተለመደው የአባገንነት ሸክም በተጨማሪ ኢትዮጵያን በቅኝ ሊገዛት እንደሞከረው ጣሊያን ህዝባችንን በየፈርጁ በዘር ከፋፍሎ በመግዛት የሀገራችንንና የህብረተሰባችንን ህልውና ጭምር የሚፈታተን ሆናል በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለነጻነትና ዲሞክራሲና ለፍትህ የሚያደርጉትን ትግል እጅግ ወሳኝ ደረጃ በመድረሱ የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ/DCESON/ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በጋራ በኖርዌይ ከሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ ጋር ለመወያየት ! ጉባኤ አዘጋጅቶል። በቦታው በክብር እንግድነት ተጋባዥ የንቅናቄው የመማክርት ጉባኤ ተባባሪ ሊቀመንበር የሆኑት አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የመማክርት ጉባኤ አባል አቶ ሌንጮ ለታ...... እርሰወም በዚህ ፕሮግራም ላይ በመገኘት እንዲሁም ሌሎችንም በመጋበዝ ታሪካዊና ወቅታዊ አገራዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ቀን ፣ ጁን 17- 2017
ሰዓት ፣ 15 00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ ፣ በቅርቡ ይገለጻል
አዘጋጅ ፣የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጭ ድርጅት በኖርዌይ
መረጃ ፣ 94254599 .....46240132
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!

No comments:

Post a Comment