የነፃነት አርበኛ የጀግናው አንድአርጋቸው ፅጌ እህት ወይዘሮ ብዙአየሁ ፅጌ ፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ሰብሳቢ በኖርዌ ዶክተር ሙሉአለም አዳም፣ እንዲሁም አቶ ዮሃንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮዽያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ዋና ሊቀመንበር ሌሎች ተጋባጅ አንግዶች በዝግጅቱ ላይ የተገኙ ሲሆን እንዲሁም በስታቫንገር ከተማ ከኢትዮጵያኖች ጎን በመቆም ሲረዱ ሲያግዙ ለነበሩ ኖርዌጂያን ድርጅቶች እና ግለሰቦች የምስጋና ወረቀት የተሰጠ ሲሆን እነሱም ሁሌም ከጎናችን እንደሚቆሙ ገልፀዋል ። በዝግጅቱ ላይ የታደሙ ኢትዮጵያኖች ይህንን መጠነ ሰፊ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮነሚያዊ ችግሮቻችንን በጋራ ሆነን ተወያይተው በመፍትሄው ሃሳብ ዙሪያ ማድረግ የሚገባውን በመመካከር ወደ ተጨባጭ ወደሆነ ተግባራዊ ስራዎች ግዜ ሳይባክን እንድንሸጋገር እና ሃገራችንን ኢትዮጵያን ከገባችበት መከራና ስቃይ ለማዳንና ለህዝባችንን ተገን በመሆን የተሻለ ስርዓት ለመገንባትና ለሂደቱ ደጀንነታችንን በተግባር ለማሳየት᎓ እንዲሁም በትግል ሜዳ ለሚገኙ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለነፃነት አርበኞች የጀግናው አንዳርጋቸው ፎቶ ባለበት ፖስት ካርድ የስብሰባው ታዳሚዎች ሰላምታቸውንና ድጋፋቸውንና ሃሳባቸውን በመፃፍ ልከዋል᎓᎓
የአንድአርጋቸው ልጆች አይፈሩም ተራራ ! ብሄራዊ ውርደት በቃ ! ላነቺ ነው ሃገሬ !
No comments:
Post a Comment