Tuesday, September 8, 2015

ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በስታቫንገር ቅርንጫፍ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በታሳካ ሁኔታ አካሄደ

DCESON Meeting in Norway
ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በስታቫንገር ቅርንጫፍ 05 09 2015 በተጠራው ስብሰባ ላይ በኖሮዌ በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያን በዝግጁቱ በመገኘት የሃገሬ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል በማለት በችግሮቻችን እና በመፍትሄው ሃሳቦች ላይ ለመወያየት እና ለኢትዮጵያ አንድነትና ዲሞክራሲ የሚደረገውን ሃገር የማዳን ጥረት ውጤታማ እንዲሆን በየአቅማቸው መጠን ለመተባበር እና ደጀንነታቸውን ለማሳየትታላቅ ህዝባዊ ውይይት አካሄደዋል᎓᎓
የነፃነት አርበኛ የጀግናው አንድአርጋቸው ፅጌ እህት ወይዘሮ ብዙአየሁ ፅጌ ፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ሰብሳቢ በኖርዌ ዶክተር ሙሉአለም አዳም፣ እንዲሁም አቶ ዮሃንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮዽያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ዋና ሊቀመንበር ሌሎች ተጋባጅ አንግዶች በዝግጅቱ ላይ የተገኙ ሲሆን እንዲሁም በስታቫንገር ከተማ ከኢትዮጵያኖች ጎን በመቆም ሲረዱ ሲያግዙ ለነበሩ ኖርዌጂያን ድርጅቶች እና ግለሰቦች የምስጋና ወረቀት የተሰጠ ሲሆን እነሱም ሁሌም ከጎናችን እንደሚቆሙ ገልፀዋል ። በዝግጅቱ ላይ የታደሙ ኢትዮጵያኖች ይህንን መጠነ ሰፊ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮነሚያዊ ችግሮቻችንን በጋራ ሆነን ተወያይተው በመፍትሄው ሃሳብ ዙሪያ ማድረግ የሚገባውን በመመካከር ወደ ተጨባጭ ወደሆነ ተግባራዊ ስራዎች ግዜ ሳይባክን እንድንሸጋገር እና ሃገራችንን ኢትዮጵያን ከገባችበት መከራና ስቃይ ለማዳንና ለህዝባችንን ተገን በመሆን የተሻለ ስርዓት ለመገንባትና ለሂደቱ ደጀንነታችንን በተግባር ለማሳየት᎓ እንዲሁም በትግል ሜዳ ለሚገኙ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለነፃነት አርበኞች የጀግናው አንዳርጋቸው ፎቶ ባለበት ፖስት ካርድ የስብሰባው ታዳሚዎች ሰላምታቸውንና ድጋፋቸውንና ሃሳባቸውን በመፃፍ ልከዋል᎓᎓
የአንድአርጋቸው ልጆች አይፈሩም ተራራ ! ብሄራዊ ውርደት በቃ ! ላነቺ ነው ሃገሬ !DCESON Meeting in Norway

No comments:

Post a Comment