Friday, August 5, 2016

ከሜሮን አንዳርካቸው ፅጌ""""""""""ሴት ማለት"""""""



የኔ ሴትነቴ ቁንጅና ውበቴ
አይደል ዳሌ ባቴ
መኩሪያ የሚሆነኝ ወንድም ወይ አባቴ
የኔ መገለጫ መሆን ጭምትነት
አይሆንም አይደለም ይለያል ሴትነት
አዎ ነኝ ሴት
የሀገር አንድ እሴት
ሆድ ብሶኝ በለቅሶ በአልችልም ስሜት
አንጀት ልቤን አሞት
ስጋዬ ፈልጎ ነፃነትን አምሮት
ወደዋላ ማልቀር ተቀምጬ ማልሞት
እኔ ነኝ ሴት ማለት!
ፍርሀት መለኪያዬ አይደለም መርበትበት
መጋባት መግባባት
በሀዘን መባባት
ወልዶ ህፃን ማቀፍ
ከልጅ ጋር መንሰፍሰፍ
ሴትነት ሲነገር
ሩህሩና ገራገር
እኩል መነጋገር
እኩል መከራከር
የዝምታ ክብር
ይቅርብኝ ወጉ አንገት መድፋት ጌጤ
የለም ይሄ ውስጤ
የኔ ሴትነቴ ከዛ ሁሉ ርቆ
ከባህል ወግ መጥቆ
ነፃነት ተናጥቆ
አንባገነን ማሸሽ
ጮሄበት መረበሽ
ይችላል ማንቕሸሽ
ጡንቻዬ ጠንካራ ብርቱ ነው አጥንቴ
ከምን ሊያግደኝ መሆን ከኔነቴ
ከማንም ሳልጠብቅ በራሴ ተጉዤ
በትከሻዬ ላይ ጠብ መንጃዬን ይዤ
ደምቼ የምሞት ቅንጣት የማልፈራ
የሚተፋን እሳት ሰደድ የምጋራ
ባሩዱን የማሸት
እኔ ነኝ ሴት ማለት !!!!
በቢሊሱማ ቢሊሱማ
በትግል ውስጥ ላላችሁ ሴት ታጋዮች በሙሉ።

No comments:

Post a Comment