Friday, August 5, 2016

ኢሳት ሬዲዮ -በኦሮሚያና በአማራ ቅዳሜና እሁድ ለተጠሩት የተቃውሞ ትዕይንቶች ዝግጅቱ እየተካሄደ ነው። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ''በአብዛኛው የኦሮሚያ ከተሞች የሰልፉ ዝግጅት በመካሄድ ላይ ነው። በአንዳንድ ቦታዎች ሰልፉን ለማደናቀፍ የስርዓቱ ታጣቂዎች አፈሳ ጀምረዋል'' ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል ሰልፉን አላውቀውም እያለ ነው። -በደብረታቦርና በባህርዳር ለቅዳሜና እሁድ የተጠሩት ሰልፎች ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገላቸው መሆኑን አዘጋጆቹ ለኢሳት ገለጹ። ባህር ዳር የጎንደሩን የነጻነት ደውል ተቀብላ ልታስተጋባ ተዘጋጅታለች። -የተለያዩ ድርጅቶች ታሪካዊ ያሉትን ጥምረት በቅርቡ ይፋ ሊያደርጉ ነው። የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ኦዴግ፡ አርበኞች ግንቦት ሰባት፡ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ተጣምረው ሊመጡ ነው። ESAT Radio 30 min Thu Aug 04 2016

No comments:

Post a Comment