Wednesday, September 9, 2015

የወያኔ ኢህአዴግ ስርአት መከላከያ …

millitary bond abay
ሰራዊት ለአባይ ግድብ መስሪያ ገንዘብ እንዲያዋጡ ለቀረበላቸው ጥሪ። እንዳልተቀበሉት ምንጮቻችን ከመከላከያ ውስጥ ገለፁ፣በምንጮቻችን መረጃ መሰረት።- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንደ አዲስ ለአባይ ግድብ መስሪያ የሚሆን በሚል ገንዘብ እንዲያዋጡ በአመራሮቻቸው ለቀረበላቸው ጥሪ። አንቀበልም ማለታቸውን የገለፀው መረጃው። ለቀረበው ጥሪ ሳይቀበሉት የቀሩበት ምክንያትም “ ባለፉት ጊዚያት በተደጋጋሚ የከፈልነውን ገንዘብ ቦንድ ይሰጣቸኋል ተብለን እስከ አሁን ድረስ ግን ሳይተገበር አንከፍልም” እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፣

መረጃው በማከል።- የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች በሰራዊቱ ውስጥ አጋጥሞ ያለውን ለአባይ ግድብ ገንዘብ አንከፍልም የማለቱ የመበታተን አደጋ። እንዴት አድርገን ለሰራዊቱ እናሳምነው በሚል በከባድ ውጥረት እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል፣

No comments:

Post a Comment