
በአንድ የብሄር የበላይነት የተዋቀረው የመከላከያ ሃይል ከውስጡ ብቅ ብቅ ባሉ የስርዓቱ
አስከፊነትና ለኢትዮጵያ የወደፊት ራዕይ የሌላቸው ከሃዲዎች መሆናቸውን የተረዱ ስርዓቱን በመተው ከነጻነት ሃይሎች ጋር በመቀላቀል
ለነጻነትና ለፍትህ እንድሁም ለሁላችንም የምትሆን ሁሉን ህዝብ በእኩልነት የምትመለከት ኢትዮጵያን ለመመስረት ቆርጠው ለመታገል ተነስተዋል፡
ዛሬ ከምን ግዜም በላይ እያንዳንዱ ኢትዮጵያ ይህ ትግል የኔ ነው የሚልበት ወቅት
በመድረሱ፡ የአርበኞች ግንቦት 7 የሚያካሄደውን የነጻነት የኢኩልነት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የመመስረትና ስፊውን ህዝብ የስልጣን
ባለቤት በሚያደርገው ትግል ውስጥ እጅግ ብዙ የሚባሉ ድሎችን በዚህ አረመንያዊ የወያኔ አገዛዝ ላይ ከህዝባዊ አመጽ አንስቶ እስከ
ትጥቅ ትግል በሚደረጉ ትግሎች ድልን በማስመዝገብ ላይ ነው።
ይህም ውጤት የመጣው ሰፊው ህዝብ ከጎኑ በሆኑና ሌት ተቀን በሚያሳየው ተሳትፎና አጋርነት
አሁንም ባገኘው ውጤት ሳይኩራራ የተያያዝነው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ
ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቱ የተከበረበት የኢኮኖሚ ብልጽግና ማህበራዊ ፍትህ የሚገኙበት የዜጎች ህይወት ደህንነትና ጥቅም የተከበረበት
ሃገር እንዲኖረው ማድረግ ይህን ራዕይ ይዞ የሚንቀሳቀሰው አርበኞች ግንቦት 7 ቀዳሚ ተልዕኮ የመንግስትና የፖለቲካ ስልጣን በሰላማዊና
ዲሞክራሲያዊ ሂደት የሚያዝበትንና የሀገሪቱ ዜጎች ምርጫ በተግባር የሚገልጽበትን ብሄራዊ ስርዓት እንዲገነባ ማድረግ ነው።
02/05/2016
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
No comments:
Post a Comment