“በወጣት አርበኞቻችን ጀግንነት፣ ጽናትና የጉሬላ ጦር ታክቲክ ክህሎት ኮርተናል። ያደረጉት ተጋድሎ ወደፊት ለሚጠብቃቸው ከዚህ የከፋ ትንቅንቅ ይበልጥ የሚያዘጋጃቸው ሲሆን የሕይወት ዋጋ የከፈሉት ሰማዕታት ጓዶቻችን ታሪክ ደግሞ ህያው ሆኖ ይኖራል።” የሚለው መግለጫው፣ የህይወት ወጋ የከፈሉትን ጓዶቹን በአሃዝ አልገለጸም።
“የአርበኞች ግንቦት 7 ደቡብ ግንባር አባላት በተግባር ያስተላለፉት መልዕክት “መሮናል፤ ዝም ብለን እንደ በግ እየተጎተትን አንታሰርም፤ የካድሬዎች የደም ጥም ማርኪያዎች አንሆንም፤ በአገራችንና በሕዝባችን ላይ የሚደርሰውን መከራ እያየን ዝም አንልም፤ ለነፃነታችን መሞት ካለብን፣ ገድለን እንሞታለን !!!” የሚል መሆኑን የሚገልጸው፣ ንቅናቄው “ ይህ ከኮስታራ ሀሞት የወጣ ድምጽ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ወገኖቻችን ድምጽ ሊሆን ይገባል።” ብሎአል።
ወታደራዊ መግለጫው አያይዞም “ትግሉን በሰሜን ኢትዮጵያና በድንበር አካባቢ ተወስኖ የማይቀር መሆኑን ይህ የመጀመሪያ ምልክት ነው፤ በሌሎች ቦታዎች ተመሳሳይ ተጋድሎዎች የሚጀመሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። በመላው ኢትዮጵያ፤ በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምስራቅና ምዕራብ፤ በዳርና በመሀል አገር እንዲሁም በከተሞችና በገጠሮች አርበኞች ግንቦት 7 ለነፃነት የሚደረገውን ፍልሚያ ያቀጣጥላል። ይህ የነፃነት ተጋድሎ አንዳንዴ ቦግ፣ ሌላ ጊዜ ደብዘዝ ይል ይሆናል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት ሳይሆን ግን አይጠፋም። “ ብሎአል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ወጣቶች ራሳቸውን ለመራር ትግል እንዲያዘጋጁ እና በየአካባቢያቸው ያለውን የጠላት ኃይል ፋታ እንዲነሱ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ አቅርቧል።
ኢሳት በጦርነቱ 20 የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን መዘገቡ ይታወቃል። መንግስት በበኩሉ ከኤርትራ በተላኩት አማጽያን ላይ እርምጃ መውሰዱንና የተወሱትን መማረኩን ገልጿል።
No comments:
Post a Comment