Wednesday, July 13, 2016

በሰሜን አሜሪካ ከሚገኘው የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የአማራ ብሔር የማንነት ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ – “ከሕዝቡ ጎን ነን”

አፋኙ የህወሃት ቡድን ሐምሌ 4 ቀን 2008 ዓ/ም በጎንደር ከተማ የሚገኙትን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የአማራ ብሔር ማንነት ኮሚቴ አባሎቻችንን በሕገ ወጥ መንገድ አስተዳደሩ ሳያውቀው ጎንደር ከተማ ውስጥ በመግባት፡፟
Gonder
1ኛ/ አቶ አታላይ ዛፌ 2ኛ/ አቶ ጌታቸው አደመ 3ኛ/ አቶ መብራቱ ጌታሁን 4ኛ/ አቶ አለነ ሻማ የተባሉትን አፍኖ የደረሱበት የጠፋ ሲሆን ኮሎኔል ደመቀን ለማፈን የተደረገው ሙከራ ኮሎኔል ደመቀ እጀን አልሰጥም በማለቱ ይህን መግለጫ እስከምናወጣበት ሰአት ድረስ ተከቦ እንደሚገኝ ያገኘነው የመረጃ ምንጭ ይገልፃል።
ይህ በዚህ እንዳለ ሰፊው የጎንደር ከተማ ሕዝብ የአማራ ማንነታችን ጉዳይ ፍትሃዊ ምላሽ ያገኛል ብለው በሰላማዊና ሕገ-መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት ጥያቄያቸውን በማቅረባቸው የኮሚቴ አባላትን አፍነው ለመውሰድ ያደረጉትን ርምጃ በመቃወም የከተማው ህዝብ በተለይም ወጣቱ ኃይል ያደረገው ርብርብና እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ መስዕዋትነት ማስከፈሉ እስከ አሁንም አፋኙን የህወሃት ቡድን ከቦ የታፈኑ ወንድሞቻችን ለማስፈታት ቆርጦ መነሳቱና ከጎናቸው መቆሙ በአማራነታችን የበለጠ ኩራት እንዲሰማን አድርጓል።
ዘራፊውና አገር መራሹ የህወሃት ቡድን ይህን የአማራ የማንነት ጉዳይ በመሣርያ ኃይል አፍኖ ዘር በማጽዳትና ዘር በማጥፋት ከ1972 ዓ/ም ጀምሮ የዘለቀበት ሲሆን አሁን እየሄደበት ያለው መንገድ ደግሞ የተነሳውን የማንነት ጥያቄ የበለጠ እንዲቀጣጠል ያደርገዋል እንጅ ሊዳፈን እንደማይችል ልናረጋግጥለት እንወዳለን። በሰላማዊ መንገድ ያቀረብነውን ጥያቄ በሰላም
መልሱን መስጠት ሲገባ እንዲህ አይነቱን ድርጊት መፈፀም ቡድኑ ጦር ጠማኝ ማለቱን አረጋግጧል። የአማራ ክልል መስተዳደርንና የአማራውን ህዝብም ምን ያህል እንደናቁትና እንደተዳፈሩት መላው የአማራ ሕዝብ ልብ እንዲለው በትህትና እንገልፃለን።
በዚህ ተንኳሽ ድርጊት በጠላት ጥይት ተመትተው ለሞቱ ሕፃናትና ወጣቶች ነብሳቸውን ይማራው እያልን ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንዲሰጣቸው በአክብሮት እንገልጻለን።
ከጎናችሁ ሆነን ይህን ግፈኛና ጠብ አጫሪ ድርጊት ባንጋፈጠም ካለንበት ሆነን ልባችን በሀዘን መሰበሩን እንድታውቁልና ከዚህ ሆነን አቅማችን በሚፈቅደው ሁሉ ለመተባበር ዝግጁ መሆናችንና ጉዳዩ እልባት ያገኝ ዘንድም ለዓለም አቀፉ ማሕበረ-ሰብ ለማሳወቅ ጥረታችን ይቀጥላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!
ሞት ለአገር መራሹ ህወሃት!!!

No comments:

Post a Comment