Tuesday, July 12, 2016

ሰበር ዜና



የህወሃት የደህንነት ግብረሃይል በአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና በቅርብ ረዳታቸው ላይ እርምጃ ለመውሰድ እቅድ መዘርጋቱን የኢሳት የደህንነት ምንጮች አስታወቁ
የአቶ ገዱና የቅርብ ረዳቶቻቸው ስልኮች መጠለፋቸውን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ አቶ ገዱም ህወሃት በእርሳቸውን እና በጓደኞቻቸውን ላይ ለመውሰድ ያቀደውን እቅድ የተመለከተ መረጃ እንደደረሳቸው ታውቋል። 
አቶ ገዱ የክልሉን ጸጥታ አይቆጣጠሩም የሚል ክስ ከህወሃቶች ሲቀርብባቸው ቆይቷል። በአቶ ገዱ የሚመራው ልዩ ሃይል ከጎንደር ከተማ እንዲወጣ ተደርጎ ፌደራል ፖሊስና መከላከያ በከተማው ተሰማርቷል
ከባድ መሳሪያ የጫኑ ተሽከርካሪዎችና ፖሊሶች ወደ ጎንደር በማምራት ላይ መሆናቸውንም የደረሰን መረጃ የማለክታል።

No comments:

Post a Comment