የኑሮ ውድነቱን በተመለከተ ብናወራው አያልቅም፡፡ የገንዘባችን የመግዛት አቅም ከቀደምት ደጋግ ዘመናት ጋር ሲነጻጸር በቀላል ግምት የዱሮዎቹ አንድ ብሮች የአሁኖቹን ከ500 እስከ 1000 ብር ይመነዝራሉ ቢባል ጨዋነትን የተላበሰ በጣም አነስተኛ ግምት ነው፡፡ የ35 ሣንቲም ቢራ አሁን በአማካይ (አንዲት ቡትሌ ቢራ በመቶዎች የሚሸጡባቸውን እነሸራተንንና ሂልተንን እንዲሁም አንዳንድ ዝጉብኞችን ትተን) 16 ብር ሲሸጥ፣ የ30 ሣንቲም ስኳር አሁን 22 ብር ሲሸጥ፣ የአምስት ሣንቲም 20 መርፌዎች አሁን ሃያ ብር ሲሸጥ፣ የ30 ብር ማኛ ጤፍ አሁን 2500 ብር ሲሸጥ፣ የስሙኒ የሥጋ ወጥ ምሣ አሁን በአማካይ 60 ብር ሲሸጥ… መቶኛ የዋጋ ንረቱን ለማወቅ የስልክህን ካልኩሌተር አውጣና ምታው፡፡ የደም ብዛትህን ግን ተቆጣጠር፡፡ ካንተ እሚብስ የለም ልጄ፤ለነገ እንድትደርስ ጠንቀቅ በል፤ “ነገም ሌላ ቀን ነው” ይባላልና፡፡

No comments:
Post a Comment