Thursday, July 14, 2016

ሰበር ዜና. . . . . በጓንጋ አሳግላ ወረዳ በትናንትናዉ እለት ዉጊያ ተደረገ!!


የነፃነት ታጋዮች ጓንጋ አሳግላ ላይ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት እስከ 12 ሰዓት 44ኛ ክፍለ ጦር ጋር ተፋልመው በትንሹ 38 ወታደሮችን ገድለው 21 አቁስለዋል

ትንቅንቁ አሁንም በመረረ ሁኔታ እንደቀጠለ ነው!!
ለግዜዉ ማንነታቸዉ ያልታወቀ የነጻነት ታጋዬች በአማራ ክልል አዋሳኝ ከተሞች ላይ በሰፈረው የትግራይ ነጻ አዉጪ ጦር ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ይገኛሉ፤
ጀግኖች የነጻነት አርበኛ ታጋዮች በትናንትናው ዕለት የአማራ ክልል አዋሳኝ በሆነ ጓንጋ አሳግላ ላይ ከ44ኛ ክፍለ ጦር ጋር ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ውግያ አድርገዉ በርካታ ቀላልና ከባድ መሳሪያዎችን እንዲሁም ሁለት የሜካናይዝድ ክ/ጦር ተሽከርካሪዎችን ማርከዉ ወስደዋል።
ይህን ጥቃት ለየት የሚያደርገዉ በአማራ ክልል በተለይም በጎንደር የተነሳዉ አመጽ በተስፋፋበት ሁኔታ ላይ መሆኑ ሲሆን እንዲህ ያለ የማስጨነቅ ዉጊያ መፈጸሙ የነጻነትን ዋዜማ ላይ እንደምንገኝ ያመላከተ ነዉ ሲሉ መረጃ የሰጡን ምንጫችን የጠቀሱ ሲሆን አንዳንድ ያነጋገርናቸዉ የዉስጥ አርበኞች ይህንን አኩሪ የሆነ ወገናዊነት የፈጸሙ የነጻነት ድርጅቶች ሐላፊነት ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃ ብለዋል ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!! 
( ጉድሽ ወያኔ )

No comments:

Post a Comment