ጎንደር በተኩስ ስትናጥ አርፍዳለች። የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ምንነት ጥያቄ አቅራቢ የኮሚቴ አባላትን ለመያዝ ከትግራይ የተላኩ የደህንነት አባላት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እጅ አልሰጥም በማለት ከደህንነት አባላት ጋር ተታኩሰዋል። እስካሁን 1 የፌደራል ፖሊስ አባልን ጨምሮ ከ3 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው። የሟቾቹን ቁጥር በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። የጎንደር ከተማ ህዝብ "ሆ" ብሎ ወደ ኮሎኔሉ ቤት በመገስገስ ላይ ነው። የፌደራል ፖሊስ አባላት ህዝቡን ለመበተን ጥረት እያደረጉ ነው። ኢሳት መረጃውን እየተከታተለ ያቀርብላችሁዋል።

No comments:
Post a Comment