የጎንደር ከተማ ህዝብ ከተማዋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።
ፌደራል ፖሊሶችና መከላከያዎች ባንኮችንና የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ብቻ እየጠበቁ ነው። የህወሃት የንግድ ቤቶችና ሰላም ባስ አውቶቡስ ተቃጥሏል። ወጣቱ አካባቢውን በድንጋይ እየዘጋ ፖሊሶች መተላለፊያ እንዳያገኙ እያደረገ ነው። ጎንደር ከዚህ ቀደም ባልታዬ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተናጠች ነው።
የወልቃይት ህዝብ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ለማገዝ በጉዞ ላይ መሆኑም ተሰምቷል። ወታደሮች ጥግ ጥግ ይዘው አካባቢውን እየቃኙ ነው። የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።
No comments:
Post a Comment