እውነትን ደፍሮ የተናገረን ሁሉ፣ ግፍና ዝርፊያ በቃኝ ያለን ሚስኪን በጥይት ቆሉት፣ አሰሩ፣ አሰቃዩት፣ ለስደትና ለችግር ዳረጉት፤ ህዝቡ ግን እንደሚመኙት ፈርቶና ተሸማቆ ጫማቸው ስር አልወደቀም።
ሃቅን ማፈን ጸሃይን እንዳትወጣ እንደመከላከል ያህል ከንቱ ድካም ቢሆንባቸው በዚህ ዘመን ሚድያና ኢንተርኔት አፍነን ከፍርድ ቀን እንድናለን ብለው ተስፋ ማድረጋቸው በቁም ቅዠት መሰቃየታቸውን አጉልቶ ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ የለውም።
ወደዱም ጠሉም ኢትዮጵያ ለልጆቿ እስር ቤት ሆና አትቀርም። ነጻነትን አፍኖ ግፍና ዝርፍያን አስፋፍቶ መኖር አይቻልም። ለግፈኞች ሃቅ ፈንጂ ነው። ዛሬ ከአድማስ እስከ አድማስ የሚነገረው ሃቅ ነገ ያጠፈቸዋል። ይህንን ሃቅ እነሱም እኛም ጠንቅቀን እናውቀዋለን!

No comments:
Post a Comment