(ዘ-ሐበሻ) በሃገር ቤት በአማራ እና በኦሮሚያ የተቀጣጠለው የሕዝብ ቁጣ በውጩ ዓለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድም በ እጅጉ እየተንጸባረቀ ነው:: ዛሬ በቦስተን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አምባሳደር አዲስ አለም ባሌማ የትግራይ ተወላጆችን ጠርተው ለማነጋገር ያዘጋጁት ሰብሰባ ኢትዮጵያውያን ሄደው በተቃውሞ እንዲበተን አድርገውታል::
በቦስተን የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች እንዳስታወቁት የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት የትግራይ ተወላጆችን ብቻ መርጠው በቦስተን ስብሰባ የጠሩት በፖስተር ላይ 4 ሰዓት ላይ ቢሆንም ስብሰባውን ግን ቀደም ብለው 2 ሰዓት ላይ ጀምረውታል:: ይህም የሕዝብን ተቃውሞ ለመሸሽና ፖስተር አይተው የሚመጡ ተቃዋሚዎችን ለመሸሽ ቢሆንም ተቃዋሚዎች ግን 3 ሰዓት ላይ ሄደው ስብሰባው ላይ አቶ አዲስዓለም ባሌማን ተጋፍጠዋቸዋል:: ከውስጥ የነበሩት የትግራይ ተወላጆች ወደ ተቃውሚዎቹ ላይ ወንበር የወረወሩ ሲሆን ከተቃዋሚውም ወገን አጸፋውን እንደተሰጠና ስብሰባው ፖሊስ ደርሶ በአስለሽ ጭስ እንደተበተነ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::
ፖሊስ የወንበር ውርወራውን ካስቆመ በኋላ የአቶ አዲስ ዓለም ባሌማ ስብሰባ እንዲቀጥልና ተቃውሚዎችም ከውጭ ሆነው እንዲቃወሙ ቢያዝም ተቃውሞው እጅግ እየበረታ በመሄዱ ፖሊስ ስብሰባው እንዲቋረጥና አዲስ ዓለም ባሌማም በቦስተን ተዋርደው እንዲሄዱ ሆኗል::
በተቃውሞው ላይ ከነበሩ ወገኖች ዘ-ሐበሻ ያነጋገረቻቸው የአይን እማኞች እንደገለጹት ለመቃወም ከሄዱት መካከል አንዲት ሴት ልጅ በሕወሓት ደጋፊዎች ወንበር ተወርውሮባት ጉዳት ደርሶባታል:: ሕክምና እያደረገችም ትገኛለች::
የኢትዮጵያውያኑን ቁጣ ለማየት ቪዲዮውን ይመልከቱ::
No comments:
Post a Comment