Wednesday, July 13, 2016

ዛሬ ብቻ በጎንደር ሕዝቡን ሲገድሉ የነበሩ 5 የፌደራል ፖሊሶች መገደላቸው ተሰማ * “18 ቀበሌ የጦር አውድማ መስሏል”

federal policeጎንደር ከተማ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ትገኛለች:: በየቦታው የጥይት ድምጽ ይሰማል:: የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚናገሩት ከሆነ ከተማዋ የሕዝብ ጩኸትና የጠምንጃ ድምጽ ከተማዋን አውከዋታል:: ወደ ሕዝብ ሲተኩሱ የዋሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይም እርምጃ እንደተወሰደ ከስፍራው የሚመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ::
እንደ ምንጮች ገለጻ ዛሬ ብቻ 5 የፌደራል ፖሊሶች በሕዝቡ እርምጃ ተወስዶባቸው በየአደባባዩ አስከሬናቸው ታይቷል:: በመንግስት በኩል ስለነዚህ 5 ወታደሮች ግድያ የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም ከሕዝቡ በኩልም ብዙዎች መገደላቸውና መቁሰላቸው ቢነገርም ክብሬን እና መሬቴን አላስደፍርም ያለው ሕዝብ አሁንም ከሕወሃት ሰራዊት ጋር በጎንደር እየተፋለመ ይገኛል ሲሉ በስልክ ያነጋገርናቸው የጎንደር አካባቢ ነዋሪዎች ይገልጻሉ::
በስልክ ያነጋገርናቸው አንድ የአይን እማኝ እንደግለጹልን |ለወልቃይት ጠለምት አማራ ማነንታቸው ሲታገሉ ከነበሩት መካከል 7 ሰዎች በጥይት ተመትተው መሞታቸውን አይተዋል::
ይህ ዜና እየተጠናቀረበት ባለበት ሰዓት በደረሰን መረጃም በጎንደር ቀበሌ 18 አካባቢ በሕወሓት ወታደሮች እና በጎንደር ወጣቶች መካከል የከረረ ውጊያ እየተደረገ ነው:: በተለይም መንግስት ከባድ መሳሪያዎችን ሁሉ በመጠቀም ላይ እንዳለ የገለጹት ምንጮች ከተማዋ የጦር አውድማ መስላለች ብለዋል:13690593_1028144947253734_5956447910984264472_n:

No comments:

Post a Comment