Sunday, August 9, 2015

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፍርድ ቤት ያልቀረቡበትን ምክንያት የማረሚያ ቤት ኃላፊ ቀርበው እንዲያስረዱ ታዘዘ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45732#sthash.YTd6sA5X.dpuf

በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው እነ ዘመነ ካሴ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሯቸውና ለሦስት ጊዜያት የተጠሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም.ባለመቅረባቸው የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኃላፊ ያልቀረቡበትን ምክንያት ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱና ምስክሩንም እንዲያቀርቡ ሌላ ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡
andargachew new picture
በሽብር ድርጊት ወንጀል ተጠርጥረው ዓቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተባቸውን የእነ ዘመነ ካሴን ክስ እየመረመረ የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደ
ታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ ለሐምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. አቶ አንዳርጋቸውን መቅረብ አለመቅረባቸውን በችሎት ሲያረጋግጥ ግለሰቡ አልቀረቡም፡፡ ለምን እንዳልቀረቡ የማረሚያ ቤት ተወካይ ቀርቦ እንዲያስረዳ ፍርድ ቤቱ ቢጠይቅም ማንም ምላሽ ሊሰጠው አልቻለም፡፡
ፍርድ ቤቱ ሌላ ትዕዛዝ ሊሰጥ ሲል ከተከሳሾቹ አንዱ ተነስተው ማረሚያ ቤቱ የተለያዩ ምክንያቶች እየሰጠ መሆኑን ገልጸው፣ አቶ አንዳርጋቸውን የያዛቸው የፀረ ሽብር የጋራ ግብረ ኃይሉ በመሆኑ ማረሚያ ቤቱ የማያቀርብ ከሆነ ለእሱ ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ተከሳሹ በመቀጠልም፣ ‹‹ተከሳሹ ፍርደኛ ነው፡፡ ፍርደኛ ደግሞ የሚኖረው ማረሚያ ቤት ነው፡፡ ለምን ማረሚያ ቤቱ እንዲያቀርብ ጥብቅ ትዕዛዝ አይሰጠውም?›› በማለት ጠይቀዋል፡፡ ከታሰሩ ሦስት ዓመታት እንደሞላቸው በመግለጽ ቤተሰቦቻቸው ‹‹የአሸባሪ ቤተሰብ›› እየተባሉ የሚያከራያቸው በማጣታቸው፣ በየቦታው ተበትነው እየተሰቃዩ መሆኑን በመናገር ፍርድ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው በአጭር ቀጠሮ ቀርበው እንዲመሰክሩላቸው ጠይቀዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ ብዛት ያላቸው ምስክሮችን እንደሚሰማና በአጭር ቀናት ማቅረብ እንደማይችል ገልጾ፣ ለጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በመኪና ሆነው አገሪቱ በልማት እያደረገች ያለውን ግስጋሴ እየጎበኙ መሆኑን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በቅርቡ መናገራቸውን የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45732#sthash.YTd6sA5X.dpuf

No comments:

Post a Comment