Sunday, August 7, 2016

የኢትዮጵያ ሕዝብ እያደረገ ያለውን ተጋድሎ የሚደግፍ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ

DC
ለወገን ትግል የአጋርነት ጥሪ

በሃገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫ የነጻነቱ ደወል እየተሰማ ይገኛል፣ከጎንደር እስከ ሃረር፣ከጋምቤላ እስከ አዳማ ህዝባችን ከጠላት ተናንቆ እየጣለም እየወደቀም ነፃነቱን ለማውጅ የተቃረበበት ግዜ ላይ ይገኛል።
እርሶስ ነጻነቶን አያውጁም? ከሆነ ህዝባችን እያደረገ ላለው ተጋድሎ አድናቆታችንን ለመግለጽ፣ደጀንነታችንን ለማሳየት፣እንዲሁም አፋኙን የወያኔ ስርዓት አቀማጥለው ያሳደጉትን እረዳቶቹን ይብላን ለናንተ ለማለት የፊታችን ማክሰኞ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት ፊት ለፊት ታላቅ ሰልፍ የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል ከተለያዩ የነጻነት ናፋቂዎች ጋር በመተባበር ያዘጋጀ ስለሆነ በቦታውም ሁላችንም በመገኘት ድምፃችንን እንድናሰማ ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል።
ቦታ ፦ Departement of State
2201 C St NW
Washington, DC. 20520

ቀን ፦ Tuesday August 9th, 2016
ሰአት ፦ 9:00 AM
የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል። dcjointtaskforce@gmail.com

No comments:

Post a Comment