Thursday, August 4, 2016

ይህ ጠቃሚ ዘዴ ለሌሎችም ሼር በማድረግ ከገጠማቸው አፈና እንዲታደጉ እናግዛቸው፡፡

‪#‎EthiopiaProtests‬ | የኢትዮጵያ ህዝብ ብሶት ላይቀለበስ መገንፈሉ ትልቅ ጭንቅ ውስጥ የከተተው የህወሓት አፋኝ አገዛዝ በሚቀጥሉት ሰዓታት አልያም ቀናቶች ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የኢንተርኔት ኮኔክሽን ሙሉ በሙሉ ለመዝጋት እየመከረ እንደሆነ መረጃዎች ስለሚያመላክቱ ፤ በተለይም ማህበራዊ ሚድያዎችን ለመጠቀም እንዳትችሉ ከታች በተቀመጡት መፍትሄዎች በመጠቀም ችግሩን መፍታት ትችላላችሁ፡፡
ይህ ጠቃሚ ዘዴ ለሌሎችም ሼር በማድረግ ከገጠማቸው አፈና እንዲታደጉ እናግዛቸው፡፡
በስልካችን ኢንተርኔት ስንጠቀም በ Operamini ብቻ ፌስቡክ እና መሰል አገልግሎቶችን መጠቀም የምንችል ሲሆን ኢንተርኔት አገልግ
ሎት ሳይቋረጥም ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎች እንደ ዋትስአፕ እና መሰል ሚዲያዎች አልሰራም እያለን ተቸግረናል ለምትሉ ይህን ችግር ለመቅረፍ ከፈለጉ የሚከተለውን መፍትሄ በመጠቀም ከችግሩ በአላህ ፈቃድ በቀላሉ መላቀቅ ይችላሉ፡
=〉 መፍትሄ -1
1. በምንጠቀምበት ስልካችን ላይ psiphon የተሰኘውን Application ከኢንተርኔት ላይ ዳውንሎድ በማድረግ መጫን
2. ይህን Application በቀላሉ በ Operamini ወይም በUc browser ማውረድ ይቻላል
3. ይህን Application ለማውረድ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ዳውንሎድ ማድረግ ይችላሉwww.apk4fun.com/int/11320/apk4fun/
4. ከላይ የተቀመጠው ሊንክ ስትጫኑ download it now from APK4Fun የሚል ምርጫ ይመጣልናል፡፡ እሱን በመጫን Application በቀላሉ ማውረድ ይቻላል፡፡
5. ይህን Application አውርዳችሁ install ካደረጋችሁ ቡሃላ ሁለት ምርጫዎችን ያመጣል፡፡ እኛ tunnel all device የሚለውን ምርጫ በመምረጥ ይህን Application መጠቀም መጀመር እንችላለን ማለት ነው፡፡
6. ይህ አፕልኬሽን ወደ ተግባር ሲገባ ሰማያዊ (Blue) P የሚል ምልክት ከስልካችን ጫፍ ላይ ያሳየናል፡፡
Grey P: connecting( ይህ ምልክት ከኢንተርኔት ጋር ተገናኝቶ ስራ ለመጀመር እየሞከረ መሆኑን ያሳየናል
Red P: not connected (ይህ ቀይ ምልክት አፕልኬሽኑ ስራ አለመጀመሩን ያሳየናል
Blue P: connected(ይህ ሰማያዊ ቀለም አፕልኬሽኑ ስራ መጀመሩን ያሳየናል
7. ይህ Application በሃገራችን የተዘጉ አፕልኬሽኖችን በሙሉ ሰብሮ በመግባት እንድንጠቀም ያስችለናል፡፡
8. ይህን Application በPlay Store ውስጥም ልናገኘው ስለምንችል ከሱ ላይ psiphon ብለን በመፈለግ ዳውንሎድ አድረገን መጠቀም እንችላለን፡፡
=〉መፍትሄ -2
ከላይ ከተጠቀሰው Application በተጨማሪ HOLA የተሰኘ Application በስልካችን ላይ በመጫን በቀላሉ የተዘጉትን አፕልኬሽን መጠቀም እንችላለን፡፡ ይህን በቀላሉ ለመጠቀም
1. Play Store ውስጥ በመግባት HOLA ብለን በመፃፍ Search አድርገን ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን፡፡
2. ይህ Application ካወረድን በኋላ ስንከፍተው በስልካችን ላይ የምንጠቀማቸውን Application ለምሳሌ Whats Up,Viber,Facebook Tango, Lite,Imo,Skype,Telegram etc.. ባጠቃላይ ሁሉንም አፕልኬሽኖች MY Apps በሚለው ምርጫ ውስጥ ተዘርዝረው ይመጣሉ፡፡
3. ሁሉንም በስልካችን ላይ የሚገኙትን Application ለማግኘት MY Apps ከሚለው ምርጫ ጎን More የሚለውን በመጫን ሁሉንም ማግኘት እንችላለን፡፡
4. ለምሳሌ Viber ከሆነ መጠቀም የፈለግነው Viber የሚለውን ስንጫን Open VIber የሚል ምርጫ ያመጣልናል፡፡ በቀላሉ Open የሚለውን በመጫን የተዘጋውን አፕልኬሽን መጠቀም እንችላለን ማለት ነው፡፡
=〉መፍትሄ -3
በተጨማሪም HOTSpot Sheild የተሰኘውንም Application በስልካችን ላይ በመጫን የተዘጉ ድረ ገፆችንም ሆነ አፕልኬኖች መጠቀም እንችላለን፡፡
ይህ Application በቀላሉ ለመጠቀም
1. Play Store ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ HOTSpot Sheild ብለን በመፃፍ ሰርች አድርገን ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን
2. ይህ አፕልኬሽን ካወረድን በኋላ ስንከፍተው Connect የሚል ምርጫ ያመጣልናል
3. እኛ የተዘጉትን Application መጠቀም ስንፈልግ HOTSpot Sheild የሚለውን በመክፈት Connect የሚለውን ስንጫን የተዘጋውን Application በሙሉ ሰብሮ በመግባት እንድንጠቀም ያስችለናል ማለት ነው፡፡
4. ይህ Application ስራ የሚጀምረው Connect የሚለው ምርጫ ተጭነን Connected ማለቱ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ይህም ከስልካችን ጫፍ ላይ አገልግሎት መስጠት ሲጀመር አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ ቀለም ምልክት ያሳየናል፡፡
እነዚህን Application በኮምፒውተራችንም ላይ በመጫን መጠቀም የምንችል መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
ማሳሰቢያ፡-እነዚህን መፍትሄዎች ከኢትዬጲያ ውጪ በየትኛውም የአለማችን ክፍሎች ያላችሁም ወንድም እና እህቶች በምትኖሩበት ሃገር እነዚህን ሚዲያዎች መጠቀም እንዳትችሉ የተዘጋ ከሆነ ከላይ በተቀመጡት መፍትሄዎች በመጠቀም ችግሩን መፍታት ትችላላችሁ፡፡
ይህ ጠቃሚ ዘዴ ለሌሎችም ሼር በማድረግ ከገጠማቸው አፈና እንዲታደጉ እናግዛቸው፡፡

No comments:

Post a Comment