የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ዘርፈ ብዙ በደሎች እንዲያቆምና ለህዝብ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ለማስገደድ ብሎም በሀገር ቤት እየተደረገ ላለው ህዝባዊ እምቢተኝነት አጋርነታችንን ለመግለፅ አርብ ኦገስት 26/2016 በፍራንክፈርት ከተማ ታላቅ ትእይንተ ህዝብ ስላዘጋጀን በመላው ጀርመን የምትገኙ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆነውን ያልተበረዘ አረንጏዴ፣ ቢጫ እና ቀዩን ባንዲራ ይዛችሁ ቢቻል ጥቁር ልብስ በመልበስ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
ሰልፉ የሚጀምርበት ሰዐት: -12:00
ሰልፉ የሚጠናቀቅበት ሰአት:-17:30
የሰልፉ መነሻ ቦታ:- ፍራንክፈርት ሀብት ቫኸ (Frankfurt Hauptwache)
ሰልፉ የሚጠናቀቀው:-ኢትዮጵያ ኢምባሲ በር ላይ
የሰልፉ አዘጋጆች:- በዲፒሀር ኢንተርቴይንመንት በጀርመን የኢትዮጵያ የባህል እና የሙዚቃ ማእከል እና በጀርመን የኢትዮጵያውያን የስደተኞች ምክር ቤት በጋራ
ለበለጠ መረጃ:- +49 15785114566
+4915218504056
+4961032904352 ይደውሉ::
No comments:
Post a Comment