Abebe Gellaw
ብዙ ወገኖቻችን መምህር ግርማ በቅን መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠታቸው በሃሰት ተከሰው መታሰራቸው አግባብ አይደለም በማለት ቁጣቸውን በማህበራዊ ድረ ገጾች በመግለጽ ናቸው። በእርግጥ በዚህ ጨቋኝ ስርአት ከፍትኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች በሃሰት ክስ እና ጥርጣሬ እስርና ፍዳ ሲደርስባቸው በርካታ አመታት አስቆጥረናል። አንዳንድ ወገኖች የጭቆናውን አስከፈነት የሚያዩት እነርሱን በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ የሚነካና የሚያስቆጣ ክስተት ሲያጋጥማቸው ብቻ መሆን አይገባውም። የህወሃቶች የግፍ ስርአት በህዝባችን ላይ ተጭኖ መከራ፣ እስራት፣ ሰቆቃና ስደት እስካላበቃ ድረስ ግፉ ይቀጥላል። ስለዚህም በግፍ የታሰሩ ሁሉ እንዲፈቱና ሰው በአገሩ ነጻነቱና ክብሩ ተከብሮለት ያለምንም መሸማቀቅ እንዲኖር በነዚህ ክስተቶች አጋጣሚ በህብረት ተነሳስተን በያለንበት ድምጻችን ከማሰማት አልፈን ለጋራ ነጻነታችን እንታገል።
መምህር ግርማና በግፍ የታሰሩ ሁሉ ይፈቱ!
No comments:
Post a Comment