መስከረም 19 ቀን 2010ዓ.ም
=======
በአርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ፣የተካሄደውን ጉባኤ አስመልክቶ አርበኛ ታጋይ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የጉባኤው የመዝግያ ንግግር ያካተተ ጽሁፍ ይዘን ቀርበናል ዝግጅቱን እንዲከታተሉ በአክብሮት እጋብዛለሁ።






”



”

እነዚህ በኮሚቴ ተደራጁ የተባሉት የትግራይ ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች ባሳደሩት ተጽእኖም አቶ አባይ ጸሀዬ ለሕክምና ከሀገር እንዲወጡ ተደርጓል ሲሉ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ባለትዳርና የልጆች እናት ከሆኑት ወይዘሮ ሳሌም ከበደ ጋር በአንድ ጣራ ስር መኖራቸው የተገለጸው አቶ አባይ ጸሀዬ ወይዘሮ ሳሌም ከበደ ከታሰሩ በኋላ በምርመራ እየወጡ ያሉ የወንጀል ድርጊቶቻቸው እንዲሁም ባለቤታቸውን መታደግ አለመቻላቸው በፈጠረባቸው ውጥረት መታመማቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ራሳቸውን በኮሚቴ ያዋቀሩት የትግራይ ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች አቶ አባይ ጸሃዬ በሕወሃት ትግል ውስጥ በመሪነት ጭምር የተጫወቱትን ሚና በመዘርዘር እንዳይታሰሩ ሲማጸኑ መቆየታቸውም ተመልክቷል። ይህ ርምጃ በሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ውስጥ ያለውን ችግር ያባብሳል፣ለጠላትም በር ይከፍታል በሚል የጸረ ሌብነት ዘመቻው እንዲቆም ሲወተውቱ መቆየታቸውም ተሰምቷል። የታሰሩትም ይቅርታ ጠይቀው በማስጠንቀቂያ እንዲፈቱም ተማጽኖ ማቅረባቸው ታውቋል።–የታሰሩትን ለመፍታት ስለመወሰኑ የታወቀ ነገር ባይኖርም እንኳን። ህኖም ክትትል ሲደረግባቸው የነበሩትና ይታሰራሉ ተብለው የሚጠበቁት ባለስልጣናትና ነጋዴዎች የሚደረግባቸው ክትትል መቆሙን እነዚሁ ምንጮች ገልጸዋል። በሀገሪቱ በሚፈጸመው ሌብነት ፊታውራሪ ተብለው የሚጠቀሱት አቶ አባይ ጸሃዬ ለሕክምና እንዲሄዱ የተፈቀደው በሌብነት ላይ የተጀመረው ዘመቻ በመቆሙና ከትግራይ ሽማግሌዎች ተጽእኖ ጋር በተያያዘ እንደሆነም መረዳት ተችሏል። አቶ አባይ ጸሃዬ ለህክምና የወጡት ወደ ጀርመን እንደሆነ ቢገለጽም በትክክል ወደየትኛው ሀገርና የህክምና ማዕከል እንደሄዱ ግን ማወቅ አልተቻለም።










አሜሪካ የኢትዮጵያ ዜጎች እንዲሰለሉና እንዲታፈኑ በሚያስችለው የደህንነት ቴክኖሎጂ መረብ ዝርጋታ እጇ አለበት መባሉ ጉዳዩን ውስጡን ለቄስ አስብሎታል። በአንድ በኩል ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ረገጣ ትፈጽማለች በማለት የምታወግዘው ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ በሌላ በኩል የጉዳዩ ተባባሪ ሆና መገኘቷ ብዙዎችን አስገርሟል። ኢንተርሴፕት የተባለው ተቋም ሚስጥራዊ ሰንዶችን በመመርመር ይፋ እንዳደርገው የአሜሪካ ብሔራዊ የደህንነት መስሪያ ቤት ኢትዮጵያ የዜጎቿን የስልክ ግንኙነትና ንግግሮችን የሚጠልፍ የቴክኖሎጂ መረብ እንድትዘረጋ ከፍተኛ የቴክኖሎጂና የስልጠና ድጋፍ አድርጓል። በአንድ በኩል በልማትና በጤና እንዲሁም በሰብአዊ ጉዳይ ላይ ብቻ እርዳታ እሰጣለሁ እያለች የምትፎክረው አሜሪካ በሌላ ሁኔታ የኢትዮጵያውያን መብት እንዲጣስና እንዲታፈን በሚያደርግ ወንጀል ተባባሪ መሆኗ ትልቅ ችግር መሆኑን ኢንተርሴፕት ዘርዝሯል። እንደ ተቋሙ ገለጻ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የስለላ መረብ መረጃ የቴክኖሎጂና የስልጠና አገልግሎት ስትሰጥ የቆየችው ሽብርተኝነትን ለመከላከል በሚል ሰበብ ነው። ይህም ሆኖ ግን የኢትዮጵያ አገዛዝ ይህን ቴክኖሎጂ ለሰብአዊ መብት ረገጣና ለአፈና እየተጠቀመበት መሆኑን አሜሪካ እያወቀች ይህን ማድረጓ አግባብነት የለውም ብሏል። ኢትዮጵያ የተቃዋሚ መሪዎችንና ጋዜጠኞችን በማሳደድና በማሰር እንዲሁም ዜጎችን በመግደል ወንጀል እየፈጸመችበት መሆኑንም ኢንተርሰፕት የተባለው ተቋም ገልጿል። አሜሪካ ለኢትዮጵያ መንግስት የስለላ መረብ የሰጠችው የቴክኖሎጂ መረብ የአንበሳው ኩራት ወይም ላየንስ ፕራይድ የተሰኘ ነው። ይህም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2002 በትንሽ የሰው ሃይል ጀምሮ በ2005 ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያደገ ነው ተብሏል። በዚህ ፕሮጀክት 8 አሜሪካውያንና 103 ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል ተብሏል። ፕሮጀክቶቹም በአዲስ አበባ፣በድሬደዋና በጎንደር ከተሞች የተዘረጉ መሆናቸው ነው የተገለጸው። በእነዚህ ፕሮጀክቶችም 7 ሺ 700 ሰንዶችና 900 ሪፖርቶች ከስለላ ስራው በኋላ የተዘጋጁ መሆናቸውን ኢንተርሴፕት አጋልጧል።