Tuesday, September 12, 2017

ዉድ ኢትዮጵያኖች ሰላማችሁ በያላችሁበት ይብዛ፣
#ሁላችንም ዶ/ር ታደስ ከርሰሞ ነን!
#Justice 4 Dr TKersemo

ዘርኛው የወያኔ አገዛዝ ላለፉት 26 ዓመታት በሀገራችንና በህዝባችን ላይ ሲፈጽም የቆየው የዘር ማጥፋት፤አፈና ና ግድያ አልባቃ ብሎት በወንጀል የተጨማለቀዉን እጁን አስረዝሞ ለነጻነት የምናደርገውን ትግል ለማኳላሸት ከተባባሪ መግስታት ጋር የማስፍራራት ዘመቻ እያደረገ ይገኛል። ለዚህም በነጻነት ታጋይ አርበኛችን በዶ/ር ታደሰ ብሩ ላይ የተመሰረተው የተቀነባበር የፖልቲካ ክስ የቅርብ ምሳሌያችን ነው። ይህ እኩይ ተግባራቸው ለነጻነት ከምናደርገውን ትግል ለአንዳፍታም እንኳን ሊያቆመን አይችልም። ይህንን በርካሽ ጥቅም ላይ የተቀነባበርር የፖለቲካ ክስ ለማክሸፍ በታላቋ ብሪታኒያና በመላው አለም ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ይገኛል። ስለዚህ በመሐበራዊ መገናኛ, (social media-facebook, twitter, እና Online petition) በየቀኑ የምናደርገው ዘመቻ በዛሬው እለት ስለምንጀምር ይህንን ዘመቻ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከ September 13, 2017 @6:00pm uk , 7pm European and 4pm Washington DC የምናደርገው ዘመቻ ላይ በትጋት እንድንሳተፉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የዶ/ር ታደስ ብሩ ኬርሰሞ ጉዳይ ያገባኛል!!
ሁላችንም ዶ/ር ታደሰ በሩ ኬርሰሞ ነን!!
የእንግሊዝ መንግስት ዘርኛ የወያኔ አገዛዝ መንግስት መደገፍ ያቁም!!

No comments:

Post a Comment