Tuesday, September 19, 2017

የራሱን እሳት በእሳት ማጥፋት የተካነበት 'ጥበበኛው' ህወሓት 9ካሳሁን ይልማ)

ለህወሓት የኦሮሞ-ሶማሌ እና የአማራ-ቅማንት ጉዳይ ልክ እንደ እሳት አደጋ ውህ ማጥፊያ ናቸው። በነሱ ሞት ራሱን ከሞት ያስነሳል። በነሱ እሳት የራሱን እሳት ያጠፋል። ነገሮችን ወደኋላ መለስ ብለን ለማሰላሰል ጊዜ ካለን:- ተቃዋሚዎች ጠንካራ ሆነው ሰላማዊ ሰልፎች በየቦታው ሲቀጣጠሉና ሕዝቡ መሰረታዊ ጥያቄዎቹን አንግቦ በድፍረት አደባባይ መውጣት ሲጀመሩ የህወሓት የመጀመርያ እርምጃ የተቃዋሚ አመራሮችን ማሰር ነው።መንግስትን የሚነቀንቅ ጥያቄ ያነሳው ሕዝብ ወዲያውኑ በሚያስገርም ፍጥነት ዋና አጀንዳውን ጥሎ መሪዎቼ ይፈቱ FREE እከሌ በሚል ዘመቻ ይጠመዳል። ይህ ሂደት ከ2 እና 3 ዓመታት በላይ በሚካሄዱ የፍርድቤት ምልልሶች ታጅቦ ይቀጥላል። ከዚያ መንግስት በይቅርታና ምህረት በሚል ታፔላ አመራሮቹን ዝቅ አድርጎ ይፈታቸዋል። ከዚያ ሕዝቡ በመሪዎቹ መፈታት ይደሰታል። አበቃ።
እናም ገዢው ሥርዓት የሚፈልገውን አጀንዳ በቅዱ መሰረት እያስኬደ ነው። ስጋት ሆኖ ህወሓትን እንቅልፍ የነሳው የኦሮሞ ተቃውሞ ሰደድ ተዳፍኗል። ኦሮሞ ያቀጣጠለውን እሳት አጥፍቶ ራሱን ሊያቃጥል የመጣ እሳት እያጠፋ ነው፣ ለዚያውም ኦህዴድን እየተማጸነ። ኦህዴድ ደግሞ ያው አለቃው ዘንድ ደጅ ይጠናል።Image may contain: 1 person, sitting, beard and indoor
አማራና ቅማንት ሪፈረንደም - ሕዝበ ውሳኔ ተብሎ በውጤቱም "ድሉ የሕዝብ ሆኗል" እየተባለ ባለበት ሰዓት ዛሬ 4 ሰዎች መገደላቸውን ሰምተናል። ጨቋኝ ስርዓት ባለበት ቦታ ሕዝበ ውሳኔ ይተገበራል ብሎ ጮቤ መርገጥ በራሱ የዋህነት ነው። 26 ዓመታት በሙሉ ደግመን-ደጋግመን የምናውቀው ከፋፋይ አረመኔ ገዢ የሕዝብ ምርጫ ይመቸዋል ብለን ካሰብን ስርዓቱ ቅቡል ነው ብለን እያመንን ነው።
ለምሳሌ አሁን ከ50 ሰው በላይ ገደለ፣ ከ50ሺ ሰው በላይ አፈናቀለ የምንለው የኦሮሞ-ሶማሌ ግጭት እኮ በሪፈረንደም ተቋጨ የተባለው የዛሬ 13 ዓመት ነበር። ስለዚህ አማራ ሕዝብ የወልቃይትን ጉዳይ በጋራ ሲጠይቅ፣ ጎንደር በዞን አትከፋፈልም ብሎ ገሞራ ሲሆን ህወሓት የውስጥ እሳት ለኩሶ የራሱን እሳት እያጠፋበት ነው።የአማራ-ቅማንት ጉዳይ በቀላሉ አይቋጭም።
ተራ መላምት አይደለም።የኦሮሞ-ሶማሌ ግጭት እንዲነሳ ምን ያህል እንደተሰራበት ለመረዳት የወያኔ የፕሮፓጋንዳ ማሽኖች ከ6 ወራት ጀምሮ በተከታታይ የጻፏቸውን ጽሑፎች መመልከት በቂ ነው።
የአማራ-ቅማንት ጉዳይም የቅማንት ተቆርቋሪ ሆነው ደጋግመው ያሰራጯቸውን መርዞች መለስ ብሎ ማንበብ ነው። ቀመሩ ያለው እዚያ ጋር ነው።
@Kassa Hun Yilma....
19/09/2017

No comments:

Post a Comment