Thursday, September 28, 2017

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)

አሁን የደረሰን ዜና ፡፡
የብአዴን የከፍተኛና የመካከለኛ አመራሮች ኮንፈረንስ ከተቀመጠለት ቀን ቀድሞ ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን ፡ በአሁኑ ሰዓት ማዕከላዊ ኮሚቴዎች፡ የቤሮ ኃላፌዎችና ምክትሎች ፡ የየዞኑ ዋና እና ምክትል አስተዳደሪዎች ፡ የዋና ከተሞች ከንቲባና ምክትል ከንቲባዎች እንዲሁም የየዞኖች የብአዴን ተጠሪዎች በባህርዳር ከተማ ግራንድ ሆቴል አዳራሽ ዝግ ስብሰባ ተቀምጠዋል ፡፡
ግራንድ ሆቴል በአሁኑ ሰዓት ዙሪያውን በፌዴራል ፖሊሶች ጥብቅ ጥበቃ እየተደረገለት ሲሆን ማንም መውጣትም ሆነ መግባት አይችልም ፡ ምንጮች ስብሰባው በ2010 የድርጅት እቅድ ለመወያየት ነው ቢሉም እቅድን ሁሉም አባል እደሚወያይበት ተነግሮ ነበር አሁንም ለሌላ ቀን ቀጠሮ የተያዘለት ሆኖ እያለ በተናጥል መደረጉ አሳማኝ አይደለም ፡ ብአዴን በተመረጡ እና በተወሰኑ አመራሮች ላይ የእስር ውሳኔ ሊያሳልፍ ይችላል የሚል መረጃ እየመጣ ይገኛል በስብሰባውም ይህን ጉዳይ ይታያል ተብሎ ይጠበቃል።Image may contain: sky and outdoor

No comments:

Post a Comment