Friday, September 15, 2017

በደዋሌ እና በሽልሌ ዞኖች ይኖሩ የነበሩ የኦሮሞ ተወላጆች በልዩ ሐይል ፖሊሶች እየተፈናቀሉ ወደ ድሬዳዋ እየገቡ መሆኑ ተነገረ። ትንሳኤ ራዲዮ


ዛሬ መስከረም 5 ቀን ከማለዳ ጀምሮ የሱማሌ ክልልን ከሚያዋስኑ ሀገሮች መሀከል ከ 2 መቶ በላይ የሚገመቱ የኦሮሞ ተወላጆች ንብረት እና ገንዘባቸዉን ሳይዙ ለአመታት ከነሩበት መንደር ተሰደዉ ወደ ድሬዳዋ በመመግባት ላይ መሆናቸዉን ካካባቢዉ የደረሰን መረጃ አመለከተ፡፤የድሬዳዋ አስተዳደር በደዋሌ የቀሩትን የኦሮሞ ተወላጆች ለማምጣት ሰባት አዉቶቡሶች መላኩ ሲታወቅ ቀደም ብለዉ የገቡት ስደተኞች እስከ እኩለ ቀን ድረስ ምንም አይነት እርዳታ ሳይደረግላቸዉ ከቆዩ በሗላ፣ ከሰአት በሗላ ወደ ጫት መሀበር ግቢ እንደተወሰዱ እና ከሰዎች ጋር እንዳይገኛኙ እንደተደረጉም ያይን እማኞች ተናግረዋል፡፤ክልሉን ለቀዉ ከወጡት ግለሰቦች መሀልም የኦሮሞ ተወላጅ ያልሆኑ እና ድርጊቱን የተቃወሙ የሌላ ብሔር ተወላጆችም እንደሚገኙበት ታዉቋል። Image may contain: 2 people, people standing and outdoor
ስደተኞቹ ሰሞኑን የሱማሌ ልዩ ሀይል በሌሎች ክልሎች በሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ እያደረጉት ካለዉን ኢሰብአዊ የማፈናቀል ድርጊት የተነሳ ስጋት ዉስጥ ገብተዉ እንደነበር ቢናገሩም፣ ምንም ሳይዘጋጁ እና ለመንገድ የሚሆናችዉ ነገር ሳይዙ በድንገት ከያሉበት እንደወንጀለኛ እየለቀሙ እንባረራለን ብለዉ አለመገመታቸዉን ተናግረዋል።አንድ ተፈናቃይ ከጎረቤቱ የቀብር ስነስርአት ላይ ተይዞ መመረጣቱንም በሀዘን ሲናገርም ተደምጧል።
በተለይ በድሬዳዋ አቅራቢያ ከምትገኘዉ ሽልሌ ዞን በርካታ ስደተኞች በእግራቸቸዉ ወደ ድሬዳዋ በመግባት ላይ መሆናቸዉ ሲታወቅ ብዙ ቁጥር ያላቸዉ የኦሮሞ ቤተሰቦች በእግራቸዉ በጉዞ ላይ እንደሆኑም ተመልክቷል። የድሬዳዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት የሱማሌ ልዩ ሀይል አባላት በድሬዳዋ ከተማ አጎራባች ቀበሌዎች አካባቢም ረብሻን ለመፍጠር ሙከራ አድርገዉ እንዳልተሳካለቸዉ ጠቅሰዉ፣ይሁን እንጂ ለወደፊት ፖሊሶቹ ከዚ በፊት የሱማሌ ክልል ይገባኛል በማለት ጥያቄ ሲያነሳባቸዉ ወደሆኑ የተወሰኑ ቀበሌዎች ተመሳሳይ ጭግርን ለመንጠር ሊሞክሩ ይችላሉ ተብሎ እየተሰጋ መሆኑን ይገልጻሉ።

15/09/2017

No comments:

Post a Comment