Tuesday, January 31, 2017
Monday, January 30, 2017
በአዲስ አበባ በ13 ወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎች ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተናል ይላሉ
በአዲስ አበባ ከወረዳ አንድ እስከ ወረዳ 13 ባሉ አካባቢዎች በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤታቸው እንደሚፈናቀሉ ከተነገራቸው በሁዋላ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል። ነዋሪዎች እንደገለጹት ከአራት ቀናት በፊት ባለስልጣናቱ መሬቱ ለአረንጓዴ ልማት ይፈለጋል በሚል ቤታቸው እንደሚፈርስባቸው ሰብስበው ነግረዋቸዋል።
http://amharic.abbaymedia.com/%
ይህን ተከትሎም ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሯል። ለረጅም ጊዜ የኖርንበትን ቀዬ ትለቃላችሁ በመባላችን ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል የሚሉት ነዋሪዎች፣ የሚፈናቀሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ አርሶአደሮችም ጭምር ናቸው።
Sunday, January 29, 2017
ለቅሶህም ለቅሶዬ ነው ! ======//========
መግቢያ፡ በየሣምንቱ ቅዳሜ በንቃት ከማዳምጣቸው የሬዲዮ አገልግሎት ሥርጭቶች አንዱና ዋነኛው በሻለቃ አብረሃም ታከለ አዘጋጅነትና አቅራቢነት የሚሰራጨውን የሠራዊቱ ድምፅ ነው ። ለምን ? ይህ ሬዲዮ የእኔና እኔን የመሰሉ የቀድሞው ሠራዊት አባል ልጆች ድምፅም ጭምር በመሆኑ ነው። ስለ ሠራዊቱም መስዋዕትነትና ተጋድሎ ሆነ ስለ ቤተሰቡ ሁኔታ በተጨባጭ ይናገራል። ሥርጭቱን ያላዳመጥኩበት ጊዜ የለም ብል አዘጋጁ ሊኮንነኝ ይችላል ። እ አ አ በወርሃ ጥቅምት መጀመሪያው ሣምንት 2014 እኔም የሬዲዮኑ የሠራዊቱ ቤተሰብ እንግዳ ሆኜ ቃለ መጠይቅ ሰጥቻለሁና ።Saturday, January 28, 2017
Subscribe to:
Posts (Atom)
