Monday, January 30, 2017

በአዲስ አበባ በ13 ወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎች ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተናል ይላሉ

በአዲስ አበባ ከወረዳ አንድ እስከ ወረዳ 13 ባሉ አካባቢዎች በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቤታቸው እንደሚፈናቀሉ ከተነገራቸው በሁዋላ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል። ነዋሪዎች እንደገለጹት ከአራት ቀናት በፊት ባለስልጣናቱ መሬቱ ለአረንጓዴ ልማት ይፈለጋል በሚል ቤታቸው እንደሚፈርስባቸው ሰብስበው ነግረዋቸዋል።
http://amharic.abbaymedia.com/%
ይህን ተከትሎም ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሯል። ለረጅም ጊዜ የኖርንበትን ቀዬ ትለቃላችሁ በመባላችን ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል የሚሉት ነዋሪዎች፣ የሚፈናቀሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ አርሶአደሮችም ጭምር ናቸው።

የከተማ እና የገጠር ነዋሪዎችን ከፋፍለው በመሰብሰብ በአንድነት አቤቱታችንን እንዳናቀርብ አድርገውናል የሚሉት ነዋሪዎች አስቸኳይ እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር ከ30-50 ሺ አባወራዎች ወይም ከ150 ሺ ያላነሱ ዜጎች ገዳና ላይ ይወድቃሉ።
በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ባሉ የገጠር ቀበሌዎች ባለፉት 5 አመታት ብቻ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በርካታ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል። የሚፈናቀሉ ዜጎች በአንድነት ቆመው ተቃውሞ ለማሰማት ባለመቻላቸው አገዛዙ ተመሳሳይ ድረጊት እንዲፈጽም እንዳደረገው ብዙዎች ይስማማሉ።
በአዲስ አበባ የሚታየው የመሬት ጥበት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ሲሆን አገዛዙም የሚፈናቀሉ ሰዎችን መሬት በሊዝ በከፍተኛ ዋጋ እየሸጠ ነው።
በቅርቡ ጥር 18 ቀን 2009 ዓ.ም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ይፋ በተደረገው 25ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለአንድ ካሬ ሜትር ቦታ 50 ሺ 250 ብር ተከፍሏል። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 2 ውስጥ ለሚገኝ 208 ካሬሜትር ቦታ ለመግዛት ለአንድ ካሬሜትር ብር 50 ሺ 250 ብር የሰጡት አቶ አብርሃም ህሉፍ ዓረፈዓይኔ የተባሉ ግለሰብ ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment