Monday, January 9, 2017

8 የወያኔ ወታደሮች በምእራብ ኢትዮጵያ በሚንቀሳቀሱ የሽምቅ ተዋጊዎች መገደላቸው ተሰማ

አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ
በኢትዮጵያ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሰብአዊ መብት ተከራካሪ የሆኑት አቶ ሃሊድ ናሲር በመንግስት ወታደሮችና በሽምቅ ታጣቂዋች ጦርነት እንደነበረ አረጋግጠዋል።

በጦርነቱም ወደ የሚቆጠሩ የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸውን ታውቋል። ከሽምቅ ተዋጊዎች ጋር ግንኙነት አላችው ያላችውን ወደ12 የሚደርሱ ነዋሪዎችን ወያኔ አስሯል።
እንደ ሰብአዊ መብት ተከራካሪው ገለጻ በርካታ ሰዎች በመንግስት ወታደሮች ተይዘው ወደ አሶሳ ከተማ እየተጫኑ እንደሆኑ መረዳት ተችላል። አቶ ናሲር በማከልም ወደ 1000የሚሆኑ ሰዎች ከዚሁ ግጭት ጋር በተያያዘ በመንግስት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቀዋል።
50 በላይ የመንግስት ወታደሮች በቅርቡ በተደረጉ ጦርነቶች መገደላቸውን የቤኒሻንጉል ነጻ አውጪ ግንባር ገልጻል። ንጹሃን ዜጎችም በነዚህ ጦርነቶች ሰለባ መሆናቸውን የግንባሩ መሪ የሆኑት አብዱላሂ አልሃዲ ገልጸዋል። ነገር ግን እንዴት እና ስንት ለሚለው ጥያቂ መልስ ሳይሰጡ ቀርተዋል።
ህዝቡ የወያኔን መንግስት በተለያዩ የኢትዮጵያ አቅጣጫዎች በትጥቅ ትግል እየተፋለመ ይገኛል።
በሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረገው የትጥቅ ትግል በቀጠለበት በአሁን ጊዜ የበላይነት ተቀዳጅቻለው በማለት ሁለቱም በየፊናቸው (የወያኔ አስተዳደርና ለነጻነት የሚታገሉ አርበኞችሲናገሩ ይደመጣሉ።

No comments:

Post a Comment